Skip to main content
x

ዜና

የህዳሴ ግድቡን ተፅዕኖና የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ የሚያጠናው ድርጅት መመርያ ተዘጋጀለት
የህዳሴ ግድቡን ተፅዕኖና የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ የሚያጠናው ድርጅት መመርያ ተዘጋጀለት
የህዳሴ ግድቡ በታችኞቹ የተፋሰስ አገሮች ላይ ሊኖረው ስለሚችለው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ተፅዕኖ፣ የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ ለማስጠናት በድርድር ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ፣ በአዲስ አበባ ለ16ኛ ጊዜ ተገናኝተው ጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. መከሩ፡፡ የጥናቱ አማካሪ ድርጅት አሠራሩን የሚመራ ረቂቅ መመርያ ላይ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡
ዘንድሮ ለዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ በጀት እንደማይኖር ተገለጸ
ዘንድሮ ለዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ በጀት እንደማይኖር ተገለጸ
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) በዚህኛው በጀት ዓመት ምንም ዓይነት ተጨማሪ በጀት እንደማይኖር ለዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ተናገሩ፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የፕሮግራም በጀት አሠራርን በደንብ እንዲተገብሩም ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልና የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ የነበሩ ግለሰብ ተከሰሱ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልና የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ የነበሩ ግለሰብ ተከሰሱ
በሶማሌ ክልል በተለያዩ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ በተለይም የፕሬዚዳንቱ አማካሪ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልና የሊበን ዞን መስተዳድር ምክትልና ዋና ኃላፊ በመሆን ይሠሩ የነበሩት አቶ መሐመድ መሐሙድ አደን ኢልሚ ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
ኦፌኮ ዓርማው ላልተፈለገ ዓላማ እየዋለበት እንደሆነ አስታወቀ
ኦፌኮ ዓርማው ላልተፈለገ ዓላማ እየዋለበት እንደሆነ አስታወቀ
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ሥፍራዎች በተደረጉ ሰላማዊ ሠልፎች ላይ የፓርቲውን ዓርማ ይዘው በማውለብለብና ፎቶ በመነሳት የተከናወኑ ተግባራት፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) እንደማይወክሉ ፓርቲው አስታወቀ፡፡
የብር ምንዛሪ ለውጥ የነዳጅ ዋጋ ያንራል የሚል ሥጋት ፈጥሯል
የብር ምንዛሪ ለውጥ የነዳጅ ዋጋ ያንራል የሚል ሥጋት ፈጥሯል
ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በብር ምንዛሪ ላይ ያደረገው የ15 በመቶ ለውጥ የነዳጅ ዋጋ ያንራል የሚል ሥጋት ፈጥሯል፡፡ ብሔራዊ ባንክ የተዳከመውን ኤክስፖርት ዘርፍ እንዲያንሠራራ ለማድረግ የብር ምንዛሪ በ15 በመቶ እንዲጨምር አድርጓል፡፡ ዕርምጃው የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎችን አስደንግጧል፡፡ የምንዛሪ ለውጡ በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ እንደሚፈጥር፣ በገቢና በአገር ውስጥ ምርቶች ላይ ዋጋ ጭማሪ በመፍጠር የኑሮ ውድነቱን ያባብሳል የሚል ሥጋት ፈጥሯል፡፡
አቶ በቀለ ገርባ በተከለከሉት የዋስትና መብት ላይ በይግባኝ ተከራከሩ
አቶ በቀለ ገርባ በተከለከሉት የዋስትና መብት ላይ በይግባኝ ተከራከሩ
ተከሰውበት ከነበረው የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ አንቀጹ ተቀይሮ እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፣ በዋስትና ጉዳይ ከዓቃቤ ሕግ ጋር ጥቅምት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ክርክር አደረጉ፡፡
የአሜሪካ ኮንግረስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ድምፅ እንዲሰጥበት ተጠየቀ
የአሜሪካ ኮንግረስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ድምፅ እንዲሰጥበት ተጠየቀ
የአሜሪካ ኮንግረስ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ በቀረበለት የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፅ እንዲሰጥበት፣ በአሜሪካ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥያቄ አቀረቡ፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾቹ ጥያቄያቸውን ለኮንግረሱ በደብዳቤ ያቀረቡት፣ ኮንግረሱ በውሳኔ ሐሳቡ ላይ ለመወያየት የያዘውን ቀነ ቀጠሮ ባልታወቀ ምክንያት በመቀየሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

ዓለም

ከ300 በላይ ሰዎች ያለቁበት የሞቃዲሾ ፍንዳታ
ከ300 በላይ ሰዎች ያለቁበት የሞቃዲሾ ፍንዳታ
በመኪና ላይ በተጠመዱ ወይም በእጅ በሚወረወሩ ቦምቦች ሶማሊያውያን ሕይወታቸውን ማጣት ከጀመሩ ሦስት አሠርታት አልፈዋል፡፡ በተለይ ከአሥር ዓመታት ወዲህ ጥንካሬውን ማሳየት የጀመረውና አሁን በሙሉ አቅሙ መንቀሳቀስ እንደተሳነው የሚነገርለት የሶማሊያው አልሻባብ ታጣቂዎች በሚፈጽሙት ግድያና ጠለፋ፣ ቀድሞውንም አቅም ያጣችውን ሶማሊያ መሰባበር ከጀመረም ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
የዶናልድ ትራምፕና የሪፐብሊካኑ ሴናተር ቦብ ኮርከር ውዝግብ
የዶናልድ ትራምፕና የሪፐብሊካኑ ሴናተር ቦብ ኮርከር ውዝግብ
ሪፐብሊካኑ ሴናተር ሪፐብሊካኑን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አካሄድህ ትክክል አይደለም ሲሉ መንቀፍ የጀመሩት፣ ትራምፕ ሥልጣን ይዘው ወራት ያህል ሳይቆዩ ነበር፡፡ የሾሟቸውን ማንሳት፣ በሥራ ላይ የነበሩትም በሥራ ገበታቸው ወር ሳያገለግሉ መልቀቅም የትራምፕን አስተዳደር የፈተነ ጉዳይ ነው፡፡
የላስ ቬጋስ ጭፍጨፋ
የላስ ቬጋስ ጭፍጨፋ
ላስ ቬጋስ ከሚገኘው ታዋቂው ማንዳላይ ቤይ ሆቴል 32ኛ ፎቅ ትይዩ ከሆነው የቬጋስ ጎዳና ላይ ጥይቱን እንደ ዝናብ አወረደው፡፡ ጥይቱ ግን እንዲሁ ጎዳና ላይ ያገኘውን ለመምታት አልሞ የሚርከፈከፍ አልነበረም፡፡
የመራሒተ መንግሥት አንገላ መርከል በምርጫ ማሸነፍና የቀኝ ጽንፈኞች ማንሰራራት አንድምታ
የመራሒተ መንግሥት አንገላ መርከል በምርጫ ማሸነፍና የቀኝ ጽንፈኞች ማንሰራራት አንድምታ
ላለፉት 12 ዓመታት ጀርመንን በመራሒተ መንግሥትነት እየመሩ ያሉት አንገላ መርከል በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ይታወቃሉ፡፡ በአውሮፓ ኅብረትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃም ተደማጭ ናቸው፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባዔ ኢራንና ሰሜን ኮሪያን ዒላማ የሚያደርገው የትራምፕ ረቂቅ ንግግር
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባዔ ኢራንና ሰሜን ኮሪያን ዒላማ የሚያደርገው የትራምፕ ረቂቅ ንግግር
አሜሪካ ቀድሞውንም ቢሆን ኢራንንና ሰሜን ኮሪያን የዓለም ሥጋት ብላ ፈርጃቸዋለች፡፡ በመሆኑም በአገሮቹ ላይ ማዕቀብ ከማስጣል አልፋ ወታደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ስትዝትና ስታስፈራራ ሁሌም ትሰማለች፡፡
አውዳሚው ኃይድሮጂን ቦምብ በኮሪያ ልሳነ ምድር
አውዳሚው ኃይድሮጂን ቦምብ በኮሪያ ልሳነ ምድር
ሰሜን ኮሪያ አጀንዳነቷ አሁንም እንደ ቀጠለ ነው፡፡ አገሮች ውዝግብ ሲገቡ፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ሲቃረኑ በድርድርም ሆነ በማዕቀብ ነገሮች የሚረግቡበት፣ ችግሮቹ እንዳለ ቢቀጥሉም የሚለሰልሱበትና የዕለት ተዕለት አጀንዳ የሚሆኑበት መጠን ይቀንሳል፡፡
ማስታወቂያ

ምን እየሰሩ ነው?

‹‹የማናውቃቸውና በነፍሳት የሚተላለፉ አዳዲስ  በሽታዎች እየመጡብን ነው››
‹‹የማናውቃቸውና በነፍሳት የሚተላለፉ አዳዲስ በሽታዎች እየመጡብን ነው››
ፕሮፌሰር ድልነሳው የኋላው፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የትሮፒካልና ተላላፊ በሽታዎች ምርምር ማዕከል ኃላፊ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከቤልጅየም መንግሥት ጋር በትብብር ሲተገብረው የቆየው የቭሊር አይዩሲ ፕሮጀክት ተጠናቆ ሁለተኛው የፕሮጀክቱ ክፍል መተግበር ከጀመረ ጥቂት ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡ ለ12 ዓመታት ሲተገበር የቆየውን ፕሮጀክት የቤልጅየሙ ገንት ዩኒቨርሲቲ ሲያስተባብረው ቆይቷል፡፡
‹‹ጫማ ውስጥ የሚገቡት ማጠንከሪያዎች እንኳን የስኳር ሕሙማንን  የደህና ሰውን እግር ይልጣሉ››
‹‹ጫማ ውስጥ የሚገቡት ማጠንከሪያዎች እንኳን የስኳር ሕሙማንን  የደህና ሰውን እግር ይልጣሉ››
ወ/ት ፀደይ ሚኬኤሌ፣ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሌዘር ኤንጂነሪንግ የአራተኛ ዓመት ተማሪ ፀደይ ሚኬኤሌ ትባላለች፡፡ ተወልዳ ያደገችውና የመሰናዶ ትምህርቷን  ያጠናቀቀችው አዲስ አበባ ነው፡፡
‹‹ማኅበሩ አማተሮች ፕሮፌሽናል ሆነው የሚወጡበት ነው››
‹‹ማኅበሩ አማተሮች ፕሮፌሽናል ሆነው የሚወጡበት ነው››
ዶ/ር ሙሴ ያዕቆብ፣ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር (ኢደማ) የተመሠረተው በ1952 ዓ.ም. ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ሁለት ሺሕ አባላት አሉት፡፡
‹‹ከመጣንበት ይልቅ የምንሄድበት መንገድ በጣም ረዥም እንደሚሆን ይሰማኛል››
‹‹ከመጣንበት ይልቅ የምንሄድበት መንገድ በጣም ረዥም እንደሚሆን ይሰማኛል››
አቶ ዳግማዊ ሰላምሳ የወወክማ ዋና ዳሬክተር አቶ ዳግማዊ ሰላምሳ የወወክማ (ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር) ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡
‹‹አምስት ሺሕ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ቢወስዱም ውጤቱ ግን ብዙም የምንኩራራበት አይደለም››
‹‹አምስት ሺሕ መምህራን የሙያ ብቃት ምዘና ቢወስዱም ውጤቱ ግን ብዙም የምንኩራራበት አይደለም››
አቶ መሐመድ አህመዲን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ የዚህን ዓመት የትምህርት ልማት ሥራን አስመልክቶ ከመስከረም 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የትምህርት ንቅናቄ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ነው፡፡
የማይዳሰሱ ቅርሶችን ለአፍሪካ ቀንድ አገሮች ሰላም ለማዋል
የማይዳሰሱ ቅርሶችን ለአፍሪካ ቀንድ አገሮች ሰላም ለማዋል
ኩሱም ጎፔል (ዶ/ር) የተባበሩት መንግሥታት ቴክኒካል ኤክስፐርት ናቸው፡፡ ምሥራቅና ምዕራብ አፍሪካን ጨምሮ በህንድ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በቬትናምና በሰሜን አውሮፓ ይሠራሉ፡፡