Skip to main content
x

ዜና

የዓለም ባንክ የ600 ሚሊዮን ዶላር ብድርና ዕርዳታ አፀደቀ
የዓለም ባንክ የ600 ሚሊዮን ዶላር ብድርና ዕርዳታ አፀደቀ
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግሥት 600 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታና ብድር ሰጠ፡፡ የብድሩ ስምምነቱን የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ዋና ዳይሬክተር ሚስ ካሮሊን ተርክ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ተፈራርመዋል፡፡
የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተጀመረ
የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተጀመረ
የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ከማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ መካሄድ ጀመረ፡፡ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከመጋቢት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በዝግ ሲመክር መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ስብሰባውን ሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. አጠናቋል፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ግማሽ ቀን ዕረፍት ካደረጉ በኋላ የምክር ቤቱ ስብሰባ በዝግ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ስለአዲሱ ፓርቲያቸው የምሥረታ ውይይት አደረጉ
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ስለአዲሱ ፓርቲያቸው የምሥረታ ውይይት አደረጉ
የኢትዮጵያውያን አገር አቀፍ ንቅናቄ መሥራቾችና የቀድሞ ሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እነ አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር)፣ ስለአዲሱ ፓርቲያቸው የምሥረታ ውይይት መጋቢት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. አደረጉ፡፡
በመንግሥትና በነዳጅ አቅራቢዎች መካከል አዲስ አለመግባባት ተፈጠረ
በመንግሥትና በነዳጅ አቅራቢዎች መካከል አዲስ አለመግባባት ተፈጠረ
አራቱ ትልልቅ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ኖክ፣ የተባበሩት፣ ቶታልና ኦይል ሊቢያ የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ያቀረበላቸውን አዲስ ውል አንቀበልም ማለታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ በመንግሥታዊ ነዳጅ ድርጅትና በግል ነዳጅ አቅራቢዎች መካከል አዲስ አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡
የግሉ ዘርፍ በባዮፊዩል ልማት እንዲሳተፉ ተጠየቀ
የግሉ ዘርፍ በባዮፊዩል ልማት እንዲሳተፉ ተጠየቀ
በባዮፊውል ልማት የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ ጥሪ ቀረበ፡፡ የአቪዬሽን ባዮፊውል ጉባዔ ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን በሒልተን ሆቴል ሲካሄድ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ መብራህቱ መለስ (ዶ/ር)፣ መንግሥት የባዮፊውል ልማት በሰፊው ለመሥራት ከፍተኛ ቁርጠኝነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ እንዲሠራ ፍላጎት እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡
ዘንድሮ መካሄድ የሚገባው የአካባቢና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ምርጫ በተመለከተ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው
ዘንድሮ መካሄድ የሚገባው የአካባቢና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ምርጫ በተመለከተ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው
ዘንድሮ መካሄድ በሚገባው የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችና የአካባቢ ምርጫን በተመለከተ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑ ታወቀ፡፡ ምርጫው መካሄድ የነበረበት በሚያዝያ ወር 2010 ዓ.ም. የነበረ ቢሆንም፣ በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ምርጫውን በወቅቱ ማከናወን አይቻልም ተብሏል፡፡
በሽብር ወንጀል የተከሰሱት የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ላይ ምስክርነት ለመስማት ቀጠሮ ተያዘ
በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ ገዳም ሁለት መነኮሳት ላይ፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ዓለም

በፈታኙ የዓለም የፖለቲካ ውጥንቅጥ ወቅት ለአራተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት የተመረጡት የቭላድሚር ፑቲን ድል
በፈታኙ የዓለም የፖለቲካ ውጥንቅጥ ወቅት ለአራተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት የተመረጡት የቭላድሚር ፑቲን ድል
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ቭላድሪሞቪች ፑቲን እ.ኤ.አ. ማርች 18 ቀን 2018 እንዲካሄድ ቀን የተቆረጠለትን ምርጫ እንደሚያሸንፉ ሳይታለም የተፈታ እንደሆነ የተረዱት ምዕራባውያን የመገናኛ ብዙኃን፣ የምርጫውን ውጤት በቅድመ ትንበያ የድምፅ መለኪያዎች ተንብየው የፑቲንን ማሸነፍ ካወጁ ቆይተዋል፡፡
ያልተጠበቀው የአሜሪካና የሰሜን ኮሪያ የመቀራረብ ጅምር
ያልተጠበቀው የአሜሪካና የሰሜን ኮሪያ የመቀራረብ ጅምር
ለዓመታት አሜሪካን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የሚያስችሉ የኑክሌር መሣሪያዎችን ሠርቻለሁ በማለትና የተለያዩ የኑክሌር አረር የተገጠመላቸው ሚሳይሎችን ስትሞክር የቆየችው ሰሜን ኮሪያ፣ ከአሜሪካ ጋር ለመነጋገር ፍላጎት ማሳየቷ ብዙዎች በግርምትና በአድናቆት የተመለከቱት ሁነት ነበር፡፡
ዓለምን ያስደመሙት የቭላድሚር ፑቲን አዳዲሶቹ የኑክሌር መሣሪያዎች
ዓለምን ያስደመሙት የቭላድሚር ፑቲን አዳዲሶቹ የኑክሌር መሣሪያዎች
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እ.ኤ.አ. ማርች 1 ቀን 2018 በዓመታዊው የምክር ቤት (ዱማ) ስብሰባ ንግግር ሲያደርጉ፣ ቃላቶቻቸውን ለማፅናት የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ምሥሎችን ለማሳየት ንግግራቸውን በተደጋጋሚ ሲያቋርጡ ነበር፡፡
ከቻይና ታላላቅ መሪዎች ጎራ የተቀላቀሉት ዢ ጂንፒንግ
ከቻይና ታላላቅ መሪዎች ጎራ የተቀላቀሉት ዢ ጂንፒንግ
የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ወደ ሥልጣን ሲመጡ ብዙም ዝና ያልነበራቸው፣ ቢበዛ ሁለት የምርጫ ዘመናትን በመንበረ ሥልጣናቸው ላይ ከመቆየት የዘለለ ሚና ይኖራቸዋል ተብሎ ብዙም አልተጠበቁም ነበር፡፡
ተስፋ የተጣለባቸው የደቡብ አፍሪካ አዲሱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ፈተናዎች
ተስፋ የተጣለባቸው የደቡብ አፍሪካ አዲሱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ፈተናዎች
ደቡብ አፍሪካ ጨቋኝና ዘረኛ ከነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ ከተላቀቀች 23 ዓመታት የሞላት ሲሆን፣ አገሪቱን ለመምራት ሲሪል ራማፎዛን አራተኛ ፕሬዚዳንቷ አድርጋ መርጣለች፡፡ ዓርብ የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ራማፎዛ አገሪቱን ለመምራት ከኔልሰን ማንዴላ፣ ከታቦ ምቤኪና ሥልጣናቸውን በግፊት ከለቀቁት ከጃኮብ ዙማ በመቀጠል አራተኛ መሪ ይሆናሉ፡፡
የጃኮብ ዙማ ፀሐይ ስትጠልቅ
የጃኮብ ዙማ ፀሐይ ስትጠልቅ
ምናልባትም ከዚምባቡዌ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ ቀጥሎ በአፍሪካ አወዛጋቢው መሪ የደቡብ አፍሪካ መሪ ጃኮብ ጌድልዬሌኪዛ ዙማ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ዙማ አልተማሩም፣ ይህንንም በኩራት ይናገራሉ፡፡ ዙማ ስድስት ሚስቶች አግብተው 22 ልጆችም ከተለያዩ እናቶች ወልደዋል፡፡ ኑሯቸውም የመሀል ስማቸውን ይመስላል የሚሏቸውም ብዙ ናቸው፡፡ ‹‹እያጠፋሁህ እስቃለሁ›› የሚባለው የመሀል ስማቸው በዙሉ ቋንቋ ነው፡፡
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

ምን እየሰሩ ነው?

የወንድማሞቹ ስጦታ
የወንድማሞቹ ስጦታ
አቶ ሙላት ፎጌ የአማጋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ድርጅታቸው በማምረት፣ በትራንስፖርትና በወጪና ገቢ፣ እንዲሁም በሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ የተሠማራ ድርጅት ነው፡፡ ድርጀቱም በቤተሰብ የተቋቋመ ነው፡፡ በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእንቦጭ አረም ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ድርጅታቸው ‹‹ለመጀመርያ ጊዜ›› የእንቦጭ አረም መከላከያ ማሽን ከቻይና ከሁለት ሚሊዮን ብር በመግዛት አገር ውስጥ አስገብቷል፡፡
የአምስት ዜና መዋዕሎች ትሩፋት
የአምስት ዜና መዋዕሎች ትሩፋት
​​​​​​​በግእዝ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ሁነኛ ሥፍራ ያለው የነገሥታት ውሎና ጉዞ የሚያትተው ዜና መዋዕል በተለይ ከ14ኛው ምዕት ጀምሮ ከሙያ መዋሉ ይገለጻል፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ባሉት ዘመናት በአክሱም ከመጀመርያ መቶ ዘመን ወዲህም ታሪክ ጠቀስ ጽሑፎች በድንጋይ ላይም ሆነ በብራና ላይ ለመጻፋቸው ማስረጃዎች አሉ፡፡
ባንክ ለማቋቋም የሰነቀው የጥቃቅንና አነስተኛ አሠሪዎች ፌዴሬሽን
ባንክ ለማቋቋም የሰነቀው የጥቃቅንና አነስተኛ አሠሪዎች ፌዴሬሽን
የጥቃቅንና አነስተኛ አሠሪዎች ፌዴሬሽን ራሱን ችሎ በፌዴሬሽን ደረጃ የተቋቋመው አምና 2009 ዓ.ም. ነበር፡፡ በመላው አገሪቱ በጥቃቅን፣ ታዳጊና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በተደራጁ 2000 ማኅበራት አማካይነት የተመሠረተ ነው፡፡
‹‹የመስተንግዶ አገልግሎት ባለው መልኩ ከቀጠለ ሆቴል መገንባቱ ዋጋ የለውም››
‹‹የመስተንግዶ አገልግሎት ባለው መልኩ ከቀጠለ ሆቴል መገንባቱ ዋጋ የለውም››
አቶ ዜናዊ መስፍን የሆቴል ባለቤቶች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ወደ መስተንግዶ (ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ) የተቀላቀሉት በአጋጣሚ ነበር፡፡ በባህር ማዶ የተከታተሉትን ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ አውስትራሊያ በሚገኘው ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተቀጠሩ፡፡ በሆቴሉ ቆይታቸው በኦዲተርነትና በዋና ኃላፊነት መሥራት ችለዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ሲሆን፣ እንደመጡ የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተቀጠሩ፡፡
​​​​​​​‹‹ሌላው ዓለም የቡናን ጥራት እንዴት መጠበቅ እንዳለበት ራሱን ሲያሻሽል እኛ ግን ራሳችንን ዘግተናል››
​​​​​​​‹‹ሌላው ዓለም የቡናን ጥራት እንዴት መጠበቅ እንዳለበት ራሱን ሲያሻሽል እኛ ግን ቆመናል ››
አቶ አማን አድነው፣ የመታድ እርሻ ልማት ድርጅት ባለቤት አቶ አማን አድነው ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ባደረገው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ አቅራቢ ድርጅት በዲኤች ኤልና እዛው በሚገኘው በኖርዝ ዌስት አየር መንገድ በኃላፊነት ደረጃ የሠሩ ሲሆን፣ በተባበሩት መንግሥታትና በኢትዮጵያ የኢሲኤክስ ቺፍ ኦፕሬተር በመሆን ሠርተዋል፡፡
‹‹አንድ ድርጅት አክሬዲቴሽን ሲሰጠው ያለምንም ጥርጥር ተቀበለው የሚል መልዕክት አለው››
‹‹አንድ ድርጅት አክሬዲቴሽን ሲሰጠው ያለምንም ጥርጥር ተቀበለው የሚል መልዕክት አለው››
አቶ አርአያ ፍሥሐ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው በ2003 ዓ.ም. ሲሆን፣ በጀት ተመድቦለት መንቀሳቀስ የጀመረው ግን በ2004 ዓ.ም. ነው፡፡ መሥሪያ ቤቱ ራሱን ችሎ እንዲወጣ የተደረገው መሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ በተጀመረበት ወቅት ነበር፡፡