Skip to main content
x

አገሪቱን ለማከም ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ ማከም በውብሸት ሙላት

አገራችን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በአለመረጋጋትና በሰላም ዕጦት ውስጥ ከርማለች፡፡ ለሰላም ዕጦቱ ወይም አለመረጋጋቱ መነሻቸው ምንም ይሁኑ ምን፣ በዚህ ሰበብ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፡፡ የአካል መጉደል ደርሷል፡፡ ንብረት ወድሟል፡፡ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡

ብሔራዊ ማንነትና ኢትዮጵያዊነትን እኩል ለማለምለም የሕገ መንግሥቱ ሚና

ሰሞኑን ለአገራችን ታላቅ የፖለቲካ አጀንዳ ሆኖ የሰነበተው የገዥው ፓርቲ፣ ኢሕአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ነው፡፡ ምርጫው ረዘም ያለ ጊዜ ወስዷል፡፡ አጀንዳነቱም ከፓርቲው አልፎ የመላው ሕዝብ ሆኗል፡፡ በተለይ ደግሞ አገሪቱን ካጋጠማት አለመረጋጋት ጋር ተያይዞም ሕዝብ አጀንዳነቱ በአንድ ፓርቲ (ግንባር) ውስጥ የሚደረግ እስከማይመስል ድረስ ከፍ ብሎ ነበር፡፡ እንዲሁም ሕዝቡ የተለያዩ ፍላጎቶችን በማሳደሩ ከእነዚህ ፍላጎቶች አኳያ በመመዘን በተለያዩ ሚዲያዎች ማንፀባረቁ አጀንዳነቱን አጠናክሮታል፡፡

በጋብቻ ላይ ጋብቻና የሴቶች በገጠር መሬት የመጠቀም መብት

በጋብቻ ላይ ጋብቻ በዓለም ላይ ካሉት አገሮች 25 በመቶ በሚሆኑት አንድ ባል ሁለትና ከዚያ በላይ ሚስት (polygyny) ማግባትን የሚፈቅዱ ሲሆን፣ አንድ ሚስት ብዙ ባሎችን ማግባት (polyandry) ብዙም የተለመደ አይደለም፡፡ አንዳንድ አገሮች አንድ ባል ሁለትና ከዚያ በላይ ሚስት እንዲኖረው የሚፈቅዱት ለእስልምና እምነት ተከታይ ማኅበረሰቦች ብቻ ነው፡፡

በሦስት መንግሥታት የወጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ሲነፃፀሩ

አገራችን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት መተዳደር ከጀመረች አንድ ወር አልፎታል፡፡ በተለመደውና በመደበኛው የሕግ አሠራር ሳይሆን ከወትሮው በተለየ አኳኋን በመተዳደር ላይ ናት ማለት ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሕግ ለመተዳደር መነሻ የሚሆኑት በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 93 ላይ ተገልጸዋል፡፡ ከእነዚህ አንዱ በተከሰተ ጊዜ የፌዴራል መንግሥቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይችላል፡፡

በንብ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ ላይ የስም ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን ያረጋገጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ

የስም ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞብኛል በማለት ክስ የመሠረቱት የቀድሞ የንብ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታፈሰ ቦጋለ ገብረ ወልድ፣ ስማቸው ስለመጥፋቱ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን በበቂ ሁኔታ በማቅረብና በማረጋገጥ ተቀናቃኛቸውን አቶ ኮሬ ባዌ ጨረቶን አሸነፉ፡፡ በስም ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል በሚል አቶ ታፈሰ የመሠረቱባቸውን የወንጀል ክስ ማስተባበል ወይም በበቂ ሁኔታ ተከራክረው መርታት ባልቻሉት አቶ ኮሬ ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት የገንዘብ ቅጣት ጥሎባቸዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት የሚመራበት የሕግ ማዕቀፍ  ሲፈተሽ

የሕዝብ ተወካይ ምክር ቤት (ፓርላማ) ዜጎች በተወካዮቻቸው አማካይነት ውሳኔ የሚሰጡበትና በመንግሥት አሠራር የሚሳተፉበት ሁኔታ የሚረጋገጥበት ዋነኛው ተቋም ሲሆን፣ ሕግ ማውጣት፣ አስፈጻሚውን መቆጣጠርና ሕዝብን መወከል  የተቋሙ ዋነኛ ተግባራት ናቸው፡፡

ዘፈቀዳዊው ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ክስ የማይመሠረትበትና የሚነሳበት አሠራር

የኢሕአዴግ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአባል ድርጅቶቹ ሊቃነ መናብርት ጋር በመሆን የግንባሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለአሥራ ሰባት ቀናት ያደረገውን ግምገማ መሠረት በማድረግ ማብራሪያና መግለጫ እንደሰጡ ይታወሳል፡፡

የወራሽ  ጠቅላይ ሚኒስትር አሿሿም ሕግ ክፍተትን የመድፈን አስፈላጊነት

በቅርቡ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲ ንቅናቄ (ደሕዴን) እና ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን አሳውቀዋል፡፡ በደሕዴንና በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚም ዘንድ ጥያቄው ተቀባይነት እንዳገኘ ይፋ ሆኗል፡፡ በቀጣይነት ደግሞ በኢሕአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡ የእነዚህን አካላት ውሳኔ ተከትሎ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ክልል ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን አዲስ አበባ የመዳኘት ኢሕገ መንግሥታዊነት

በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው የተከሰሱ እንዲሁም ጥፋተኛ ተብለው ፍርደኞች የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ ከማረሚያ ቤት ወጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉትና መደበኛ አድራሻቸው በየክልሉ የሆኑት በርካታ ናቸው፡፡ ለነገሩ ክሳቸው ያልተቋረጠ ወይም በይቅርታ ያልተለቀቁ ነገር ግን የወንጀል ድርጊቱን ፈጽመዋል በተባለበት ወቅት አድራሻቸው ክልሎች ውስጥ የነበሩ በርካታ ተከሳሾች ጉዳያቸው አዲስ አበባ በሚገኙ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በመታየት ላይ ነው፡፡

የሕዝብ ቆጠራ ሕገ መንግሥታዊ አንድምታው

አራተኛው ዙር የሕዝብ ቆጠራ በቅርቡ የሚካሔድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ቀድሞ ከተከናወኑትም የተሻለ ጥራት እንዲኖረው በቆጠራው የሚሰማሩትም ይሁኑ ተቆጣጣሪዎቹ ለእዚሁ አገልግሎት ሲባል ጥቅም ላይ የሚውሉ ኮምፒውተሮችን እንደሚጠቀሙ ይፋ ሆኗል፡፡ የሚሰበሰበው መረጃ የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ለማድረግ ያግዛል፡፡ ኮምፒተሮቹ ላይ የሚጫኑት ፕሮግራሞች ላይ ስህተት ከሌለ ወይም ካልተፈጠረ በስተቀር በወረቀት ላይ ከሚሠራው እንደሚሻል ዕሙን ነው፡፡