Skip to main content
x

ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመቱ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት ከጠቅላላ የአገልግሎት ሽያጭ 18.4 ቢሊዮን ብር ማስገባቱን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው እንደገለጸው፣ ከጠቅላላ ገቢው 13.2 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱንም ገልጿል፡፡ የኩባንያው ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ እንደጠቀሱት፣ በግማሽ ዓመቱ ከ15 በላይ አዳዲስ ተጨማሪ አገልግሎቶችን በመጀመሩ ገቢው 18.4 ቢሊዮን ብር ቢደርስም ቀደም ብሎ ካደቀው የገቢ መጠን አኳያ ማሳካት የቻለው 94.5 በመቶውን ነው፡፡

ባንኮችን ያስተሳሰረው የክፍያ ሥርዓት ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ አንቀሳቅሷል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ሁሉንም የግልና የመንግሥት ባንኮች የአክሲዮን ባለቤት በማድረግ የተቋቋመው ኢትስዊች ኩባንያ፣ የሁሉንም ባንኮች የኤቲኤም ማሽኖች በማጣመር የክፍያ ሥርዓትን ለማስፋፋት መንቀሳቀስ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ 

የመንግሥት ቁጥጥር በመዳከሙ በልኬት መሣሪያዎች የሚፈጸም ብዝብዛ ተባብሷል

በግብይት ሥርዓት ውስጥ ሚና ካላቸው አሠራሮች መካከል የልኬት መሣሪያ ወይም ሚዛን ይጠቀሳል፡፡ የልኬት መሣሪያዎች በሻጭና በገዥ መካከል የሚደረገውን  ግብይት የመዳኘት ድርሻ አላቸው፡፡ እነዚህ የልኬት መሣሪያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ  የሚያገለግሉ የጋራ ቋንቋ ለመናገር የሚያስችሉ ናቸው፡፡ ዳኝነታቸው አወንታዊ የሚሆነው ግን መሣሪያዎቹ በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውሉ ነው፡፡

ምርት ገበያ ከፍተኛ የሰሊጥና የቡና ግብይት ማከናወኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2010 ግማሽ በጀት ዓመት 317,607 ቶን የግብርና ምርቶች ያገበያየ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 133,818 ቶን ቡና በማገበያየት ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ በማስመዝገብ ቀዳሚውን ድርሻ መውሰዱ ተገለጸ፡፡ 

የምንዛሪ ለውጡ ምስቅልቅሎሽ

መንግሥት የብር የመግዛት አቅም ከዶላር አኳያ በ15 በመቶ እንዲቀንስ በመወሰን ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም በርካታ የገበያ ውዥንብር ተፈጥሯል፡፡ እንደ መንግሥት ማብራሪያ፣ የተደረገው ለውጥ እንዲያመጣ ከሚጠበቁበት መሻሻሎች አንደኛው የአገሪቱን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪ ማድረግ ነው፡፡

ለደሃ አገሮች ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ካልተተገበረ የኑሮ ልዩነት እንደሚባባስ ተመድ አስጠነቀቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ትንታኔ መሠረት፣ አብዛኞቹ በድህነት ውስጥ የሚገኙ 47 በኢኮኖሚ ኋላ የቀሩ አገሮችን ከኢኮኖሚ ለመደገፍ የበለፀጉ አገሮች ቃል ቢገቡም፣ በዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት መዳከም ሳቢያ ለመስጠት የገቡትን ቃል ከማክበር ሲያፈገፍጉ ይታያሉ፡፡ በዚህ ሳቢያም ልዩ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚገባቸው ድሆቹ አገሮች እ.ኤ.አ. በ2030 መጨረሻ ዕውን እንዲሆኑ የተቀመጡትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ያወጣቸውን ዘላቂ የልማት ግቦች የማሳካት ዕድላቸው የመነመነ ስለመሆኑ አስጠንቅቋል፡፡

ለአሰላ ብቅል ፋብሪካ ግዢ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ቀረበ

የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበር የአሰላ ብቅል ፋብሪካን ከመንግሥት ለመግዛት 1.3 ቢሊዮን ብር የመግዣ ዋጋ አቀረበ፡፡ ሰኞ የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተከፈተው ግልጽ ጨረታ፣ ከኅብረት ሥራ ማኅበሩ በተጨማሪ ሌሎች ሦስት ኩባንያዎች አብረው የመጫረቻ ዋጋቸውን አቅርበዋል፡፡ ሁለተኛውን ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው የባቫሪያ እህት ኩባንያ የሆነው ማልት አፍሪካ የተባለ ድርጅት ሲሆን፣ 42 ሚሊዮን ዶላር የግዢ ዋጋ አቅርቧል፡፡ ባቫሪያ የሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማኅበር ከፍተኛ ባለአክሲዮን እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበር ለአሰላ ብቅል ፋብሪካ ግዢ ከፍተኛውን ዋጋ ሰጠ

የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበር አሰላ ብቅል ፋብሪካን ለመግዛት 1.34 ቢሊዮን ብር ዋጋ ሰጠ፡፡

ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተከፈተው የጨረታ ሰነድ መሠረት ሦስት ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡ እነርሱም ካሊፕሶ አግሪ ቢዝነስ፣ ሶፍሌት ኢትዮጵያ እንዲም ማልት አፍሪካ ናቸው፡፡

የተምች ወረርሽኝ በዚህ ዓመት ከፍተኛ አደጋ መደቀኑ ተገለጸ

ምንጩ ከወደ ፓስፊክ አገሮች፣ ማዕከላዊ አሜሪካ ከመሆኑም በላይ የአሜሪካ የፀደይ ወራት ስያሜ በመያዝና በዩኤስ አሜሪካም ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ የሚጠቀስለትና ‹‹ፎል አርሚዎርም›› በመባል የሚጠራው የተምች ወረርሽኝ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገሮችን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አዳርሶ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም  ካለፈው ዓመት የበለጠ ጥፋት በኢትዮጵያ ሊያስከትል እንደሚችል ተገምቷል፡፡ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስአይዲ) አማካይነት በሚመራው ፊድ ዘ ፊውቸር የኢትዮጵያ እሴት ሰንሰለት ፕሮግራም ቺፍ ኦፍ ስታፍ ኢያን ቼስተርማን ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ ወቅት እንዳስታወቁት፣ የተምች ወረርሽኙ የአገሪቱን ሰብሎች በመላመዱና የአየሩ ጠባይ ለመራባት ምቹ ስለሆነለት በዚህ ዓመት ሊያደርስ የሚችለው ጥፋት ካለፈው ዓመት ይልቅ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

በአዳማ ከፕላስቲክ የውኃ ጠርሙሶች ቪላ ቤት ተገነባ

ሲምኮን ቴክኖሎጂስ የተባለ አገር በቀል ኩባንያ፣ አገልግሎታቸውን የጨረሱ  የውኃ ማሸጊያ ፕላስቲክ ጠርሙሶችን በመጠቀም ያስገነባውን ዘመናዊ ቪላ ቤት ለአገልግሎት አበቃ፡፡ ኩባንያው ለአገሪቱ እንግዳ የሆነውንና ለአካባቢ ጥበቃ ፋይዳ ያለውን አሠራር በመጠቀም፣ ከተጣሉ የውኃ መያዣ ፕላስቲክ ጠርሙሶች የተሠራው ሞዴል ቪላ ቤት የተገነባው በአዳማ ከተማ ነው፡፡ የፕላስቲክ ጠርሙስ ቪላ ቤቱ ሐሙስ፣ የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሕዝብ ዕይታ ይፋ በተደረገበት ወቅት እንደተገለጸው፣ በመቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ቪላ ቤት፣ ለግንባታው ከ53 ሺሕ በላይ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ጠይቋል፡፡ የቪላ ቤቱን ግንባታ ለማጠናቀቅ የጠየቀው አጠቃላይ ወጪ 345 ሺሕ ብር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ግንባታውን ለማጠናቀቅም ሦስት ሳምንታት ብቻ እንደፈጀ ኩባንያው አስታውቋል፡፡