የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሌሎች ባንኮች ጋር በጋራ በኔትወርክ በመተሳሰር የየትኛውም ባንክ ደንበኞች ሲገለገሉበት የቆዩትን የካርድ ክፍያ አሠራር ለማቋረጥ የተገደደው ተመሳስለው በተሠሩና በተጭበረበሩ ካርዶች ምክንያት እንደነበር ብሔራዊ ባንክ ይፋ አደረገ፡፡   

  • በበጀት ዓመቱ የ43 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶች ለኮንትራክተሮች ተሰጥተዋል

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከ17.6 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ 19 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማስገንባት ከ12 ኮንትራክተሮች ጋር ስምምነት በመፈረም፣ በበጀት ዓመቱ የተፈረሙ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ቁጥር 50 አደረሰ፡፡

በአዲስ አበባ የሜትር ታክሲዎችን ከቀረጥ ነፃ በማስገባት ለሚንቀሳቀሱ ባለንብረቶች የሽያጭ አገልግሎት የሰጠው የቻይናው ሊፋን ሞተርስ ኩባንያ፣ እስካሁን ለሸጣቸው 825 ሊፋን ሥሪት ሜትር አገልግሎት ድኅረ ሽያጭ የጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ይፋ አድጓል፡፡

ንብ ኢንሹራንስ ከ16ቱ የግል መድን ድርጅቶች ኢንዱትሪውን በመቀላቀል ቀደምት ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡ ኩባንያው የራሱን የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ለመገንባት ዕቅዱን ይፋ ካደረገ ከ12 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡

Pages