እንደ ሮይተርስ ዘገባ፣ በፍጥነት ቁጥሩ እየጨመረ የመጣው የዓለም ሕዝብ እነዚህ መሠረታዊ ፍላጎቶቹ ካልተሟሉለት በትንሹ ሦስት ቢሊዮን ሕዝብ የድህነት አረንቋ ውስጥ ይወድቃል፡፡ እ.ኤ.አ በ2040 የዓለም ሕዝብ ቁጥር ዘጠኝ ቢሊዮን ይደርሳል ተብሎ የተተነበየ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት መካከለኛ ገቢ ያለው ሦስት ቢሊዮን ሕዝብ ለፍጆታ ዕቃዎች ፍላጎት ስለሚኖረው አቅርቦት ሊያንስ ይችላል ይላል ሪፖርቱ፡፡
ሌላው ቀርቶ እ.ኤ.አ በ2030 ዓለም አሁን ካለው 50 በመቶ ተጨማሪ ምግብ፣ 45 በመቶ ኃይልና 30 በመቶ ውኃ ይፈልጋል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ እየገዘፈ በሚታይበት ጊዜ ደግሞ አቅርቦት ላይ ተፅዕኖ ይፈጠራል የሚለው ሪፖርቱ፣ ይህንን ለማሳካት ካልተቻለ ግን ሦስት ቢሊዮን ሰዎች ለድህነት ይጋለጣሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የዓለም ሕዝብ ቁጥር ሰባት ቢሊዮን ደርሷል፡፡


