በግማሹ በበጀት ዓመቱ ከላይ ቁጥራቸው የተገለጸውን ሰዎች በአዲስ በማደራጀት፣ ነባሮችን በማጠናከርና በመንግሥት ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት፣ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መቻሉን ዘገባው ያስረዳል፡፡
የሥራ ዕድሉ የተፈጠረላቸው በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በእንጨትና ብረታ ብረት፣ በከተማ ግብርና፣ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና በመንግሥት የግንባታ ፕሮጀክቶች አማካይነት መሆኑን ዘገባው ያስረዳል፡፡


