Thu05172012

Go to :English Edition

Back Home

ከ1.8 ሚሊዮን ሔክታር በላይ መሬት በተፈሰስ ልማት እየለማ ነው

  • PDF

በደቡብ ክልል ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሔክታር መሬት ላይ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የክልሉ መንግሥት ማስታወቁን ዋልታ ዘገበ፡፡

የተፋሰስ ልማቱ በመካሄድ ላይ የሚገኘው በክልሉ ለከፍተኛ የመሬት መራቆት በተጋለጡ የገጠር ቀበሌዎችና ወረዳዎች ውስጥ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል፡፡ እንደዘገባው ከሆነ፣ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች 6,942 ንዑስ የተፋሰስ ልማት ዕቅዶች የተዘጋጀው በየቀበሌው በተደራጁ የልማት ሠራዊቶች አማካይነት ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

በክልሉ ከሦስት ሺሕ በላይ በሚሆኑ ቀበሌዎች ውስጥ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የተፋሰስ ልማት ቁጥራቸው አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡