Thu05172012

Go to :English Edition

Back Home

የውጭ የሥራ አገናኝ ኤጀንሲዎች ከብልሹ አሠራር እንዲታቀቡ ተነገራቸው

  • PDF

ወደ ውጭ አገሮች በተለይም ወደ ዓረብ አገሮች ዜጎችን ለሥራ የሚያሰማሩ የሥራ አገናኝ ኤጀንሲዎች፣ ከብልሹ አሠራሮችና ከኪራይ ሰብሳቢነት ራሳቸውን እንዲያፀዱ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳሰቡን ኢዜአ ዘገበ፡፡

በሥራና ሠራተኛ ማገናኘት አገልግሎት አዋጁና በለውጥ ሠራዊት ግንባታ ላይ ለኤጀንሲዎቹ የተዘጋጀው ሥልጠና ሲከፈት፣ ሕገወጥነትና ኪራይ ሰብሳቢነትን በሚያራምዱ ኤጀንሲዎች እየተፈጸሙ ያሉ ችግሮችን መታገል እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ በተለይም በዓረብ አገሮች በሚገኙ ዜጎች ላይ የሚያጋጥሙን የመብት ጥሰቶችና ተያያዥ ችግሮችን ለመቀነስ የተጠናከረ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ዘገባው ያስረዳል፡፡

ኤጀንሲዎች ችግሩን ለመከላከል በአዋጅ የተደነገጉትን አሠራሮች ተከትለው መሥራት እንደሚገባም ይገባቸዋል ተብሏል፡፡ ዜጎችም ወደ ውጭ ሲሄዱ የመብት ጥሰት እንዳያጋጥማቸው ሕጋዊ ካልሆኑ ኤጀንሲዎች ጋር በምንም ዓይነት መንገድ የሥራ ቅጥር ውል መዋዋል እንደሌለባቸውም ሚኒስትሩ ማስገንዘባቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል፡፡ ችግሩንም ለመከላከል ጉዳዩ ከሚመለከተው ሚኒስትሮች የተውጣጣው ብሔራዊ ኮሚቴ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን በዘገባው ተገልጿል፡፡