አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የዳሸን - አርሰናል መሠረታዊ የእግር ኳስ ሥልጠና ተካሄደ

በታዳጊዎች የእግር ኳስ ሥልጠና ከእንግሊዙ አርሰናል ክለብ ጋር የተጣመረው ዳሸን ቢራ፣ የሦስተኛ ዙር የአሠልጣኝነት ሥልጠና የካቲት 1 እና 2 ቀን 2009 ዓ.ም. አከናወነ፡፡ ከተለያዩ ባለድርሻዎች የተወጣጡ 32 አሠልጣኞች በተሳተፉበት የንድፈ ሐሳብና የተግባር ትምህርት፣ በበሻሌ ሆቴልና በንግድ ባንክ እግር ኳስ ክለብ ሜዳ በአርሰናል እግር ኳስ ማሠልጠኛ አካዴሚ ባልደረባዎች፣ ሳይመን ማክማንስና ካርላን ኤድጋር ተሰጥቷል፡፡ የታዳጊ ወጣቶች አሠልጣኞች ከመሠረታዊ የእግር ኳስ ቴክኒኮች ባሻገር፣ የእንግሊዙን ከአርሰናል የአጨዋወት ዘይቤ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ትምህርት እንደቀሰሙ ተናግረዋል፡፡ (በዳዊት ቶሎሳ)