አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

ሐሙስ ታኅሳስ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት በአዲስ አበባ ሒልተን የአገሪቱን የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ባሰባሰበ ፕሮግራም የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ጌታሁን ናና፣ ለኢንዱስትሪው ዕድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል። በዚህ የዕውቅና ፕሮግራም ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉና የባንኩ ምክትል ገዥዎች ጭምር ታድመዋል። የሁሉም ባንኮች መሪዎች በተገኙበት ይህ ፕሮግራም አንጋፋ የሚባሉትን የባንክ መሪዎች ያሳተፈም ነበር። ምሽቱ እንደ ታሪካዊ ቀን የተቆጠረ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክና የባንኮች መሪዎች በነፃነት ሲነጋገሩ ያመሹበት፣ ተደጋግፎና ተመካክሮ መሥራት የሚቻል ስለመሆኑ ሐሳብ የተለዋወጡበት፣ የኢንዱስትሪውን የቆየ ታሪክና የታለፉትን መንገዶች በማስታወስ የልምድ ልውውጥ የተደረገበት ምሽት ነበር። የዕውቅና ፕሮግራሙ በባንኮች ማኅበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ለአቶ ጌታሁን የጣት ቀለበትና መጠኑ
ባይገለጽም የገንዘብ ሽልማት የተሰጠበት ነበር።