Skip to main content
x
‹‹በቋንቋችሁ ‹ኮሚቴ› የሚለውን የሚተካ ቃል የላችሁም እንዴ?››

‹‹በቋንቋችሁ ‹ኮሚቴ› የሚለውን የሚተካ ቃል የላችሁም እንዴ?››

የዑጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ፣ የዓድዋ ዩኒቨርሲቲ ፎር ፓን አፍሪካን ስተዲስ በዓድዋ ከተማ ለመመሥረት የመሠረት ድንጋይ በተቀመጠበት አጋጣሚ የተናገሩት፡፡ ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ በክብር እንግድነት በተገኙበትና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር የመሠረት ድንጋይ ባስቀመጡበት መርሐ ግብር ላይ ለንግግራቸው መንደርደሪያ ያደረጉት፣ የመድረኩ አጋፋሪዎች በተደጋጋሚ ‹‹ኮሚቴ›› የሚለውን ቃል መጠቀማቸውን ሰምተው ‹‹ለምን? አማርኛ የለውም እንዴ›› በማለት ብቻ ሳይወሰኑ፣ በቋንቋችን ቃሉን የሚተካ አለንም ብለዋል፡፡ በዲስኩራቸው የአፍሪካውያንና የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ኩራት በሆነው ‹‹በተቀደሰችው›› ምድር ዓድዋ የፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ መገንባቱ እውነታውን የሚያሳይ የታሪክና የዕውቀት ማዕከል እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በበኩላቸው ‹‹የዓድዋ የፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ገድል ብቻ ሳይሆን የመላው አፍሪካ የቅኝ ግዛት ታሪክ በዚህ የማስተማርና የምርምር ሥራ ይዳሰሳል ብዬ አምናለሁ›› ብለዋል፡፡