Skip to main content
x
‹‹ጎራዴ›› ዓሳ

‹‹ጎራዴ›› ዓሳ

በጣና ሐይቅ 28 የዓሳ ዝርያዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 21 የአገሪቱ ብርቅዬ ዝርያዎች ናቸው፡፡ በጣም የሚታወቀው በጣና ሐይቅ ውስጥ የሚገኘው የሲፕሪኒዴ ቤተሰብ ዝርያ የሆነው የዓሳ ዓይነት ላቢዎባርበስ ወይም ጎራዴ ነው፡፡

ላቢዎባርበርስ አኪዩቲሮስቲሪስ መካከለኛ መጠን ያለው (ትልቁ የርዝመት መጠን 411 ሚሊ ሜትር) በጣም ርቀት በሆነ የውኃ ጥልቀት የሚገኝ (በሰውነት ከጭንቅላት በታች በሆነ ርዝመት በሚለካ ጥልቀት) እና ቀጭን ዝርያዎች ያሉት አልፎ አልፎ በማጅራቱ ላይ ጋማ ያለው (በብዛት የሚራባ) ዝርያ ነው፡፡ ዝርያዎቹ ከ32 እስከ 411 ሚሊ ሜትር ርዝመት ያላቸው ናቸው፡፡ ጭንቅላታቸው በአማካይ ረጅምና ቀጭን ሲሆን ትንሽ የጭንቅላት ጥልቀትና ጎበጥ ያለ አንገት አላቸው የጭንቅላታው ዘንበል በማለት በአማካይ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ የዓይናቸው ጉድጓድ ተመጣጣኝ ርቀት ያለው ሆኖ በአማካይ በጣም ሰፊ ነው፡፡ የዓይናቸው ሽፋን ወደ ውስጥ የጠለቀና ትንሽ ነው፡፡ የታችኛው መንጋጋቸው በአማካይ ረጅምና ከላይኛው መንጋጋቸው ጋር እኩል ነው፡፡ በአብዛኛው በዝርያዎቹ መካከል ይህ ይታያል፡፡

የአፋቸው ጠርዝ በከፊል የተቆለመመና ሰፊ ነው፡፡ ቀጫጭን ከንፈሮች እንዲሁም የታችኛው ከንፈር ባለመስመር ነው፡፡ የቆዳ ቅርፊታቸው በጣም አጭርና በአማካይ ቀጫጭን ናቸወ፡፡ የኋለኛው ባለሸንተረር ክንፍ በአማካይ ከ31 እስከ 36 መስመር ያለው ነው፡፡ ከጀርባ እስከ ኋለኛው መስመር ድረስ በአማካይ ከፍተኛ (5.5 እስከ 7) ዙሪያው ስኬል ብዛት (24 እስከ 26) ይሆናል፡፡

በሕይወት ያሉ ዝርያዎች በጣም ቀላል ቀለማቸውም ነጭ ብርማ ነው፡፡ ጀርባቸው በመጠኑ ጠየም  ያለ (ግራጫ ብርማ ቀለም) ነጭ፣ በአብዛኛው ጊዜ የፔክቶራልና አልፎ አልፎ የካውዳል የመንሳፈፊያ እግሮች (ፊኖች) ከመሠረታቸው ፎዝ ወይም ቀይ ይሆናሉ፡፡ በአልኮል ውስጥ ቀላል የሆነው ቀለም በመጠኑ ጠየም ያለ ጀርባ ሆኖ ይስተዋላል፡፡ ዋነኛው ቀለም ቀለል ያለ ቢጫማ ቡኒ ነው፡፡

  • አበበ ጌታሁን (ፕሮፌሰር) ጽፈውት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ለመታሰቢያ ቴምብር ያሳተመው