ከኬ.ኬ.ኬ "መምረጥ አትችሉም" እስከ ለኋይት ሃውስ መመረጥ
በጌታቸው ንጋቱጥቅምት 25 ቀን 2001 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የሠዓት አቆጣጠር ከምሽቱ አንድ ሠዓት ጀምሮ በኢትዮጵያ የሚኖሩ አሜሪካዊያን በአንድ አሜሪካዊ ወዳጃቸው ቤት ተሰባስበዋል፡፡ ሁሉም አሜሪካዊያን አይደሉም፤ ከሌሎች አገራትም ለተለያዩ ሥራዎች አዲስ አበባ የመጡ ሁሉ በዚህ ቤት ተሰባስበዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ የአሜሪካ ኘሬዚዳንታዊ ምርጫን በመከታተል አዲስ አበባ ሆነው የመረጡትን ተወዳዳሪ ለመደገፍ ነበር፡፡ "መምረጥ አትችሉም" የሚባሉ ጥቁሮች ለመመረጥ ተወዳድረው ያሸነፉበት ምርጫ ለማየት ነበር ዝግጅቱ፡፡