Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የምርጫ 97 የቅንጅት የፓርላማ አባላት...
የምርጫ 97 የቅንጅት የፓርላማ አባላት... Print E-mail
Sunday, 23 March 2008
የምርጫ 97 የቅንጅት የፓርላማ አባላት እነ ወ/ሪት ብርቱካንን ወቀሱ

የምርጫ 97 የቅንጅት የፓርላማ ተመራጮች በቀድሞ የቅንጅት አመራሮች የተመሰረተው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የቀድሞውን ቅንጅት እንደማይወክል ገለፁ፡፡

የፓርላማ አባላቱ ለሪፖርተር ጋዜጣ በላኩት ጋዜጣዊ መግለጫ በቅንጅት አመራር የተፈጠረውን የሀሳብ ልዩነት ለመፍታት የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት አንድ ቀን እንኳን ሳይካሄድ በዲሲኘሊን ግድፈት የታገዱት አምስት የአመራር አባላት ጥቂት መሰሎቻቸውን በማሰባሰብ አዲስ ፓርቲ በመመሥረት ላይ መሆናቸውን ገልፆ ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡

እነ ወ/ሪት ብርቱካን አዲስ ፓርቲ ማቋቋማቸው እንዳላሳዘናቸው የጠቆሙት የፓርላማ አባላቱ እነሱን ያሳዘናቸው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ መስራቾች ቅንጅትን በማፍረስ አዲስ ፓርቲ እየመሰረቱ ዛሬም ቅንጅት ነን፣ መሪያችንም ኢንጅነር ኃይሉ ናቸው የሚል መግለጫ መስጠታቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የፓርላማ አባላቱ ባወጡት በዚሁ ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ላይ የቅንጅት ስምና የምርጫ ምልክቱ ለሌላ አካል አላግባብ ሲሰጥ የእነ ወ/ሪት ብርቱካን ቡድን ዝም ብሎ ቆይቶ አዲስ ፓርቲ ማቋቋሙ ተገቢ ድርጊት አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡ አዲስ ስም ሰጥቶ ፓርቲው እንዲንቀሳቀስ ማድረግ የሚቻለውም በጠቅላላው ጉባዔ ውሳኔ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መስራቾች የመመስረቻ ፅሁፍና የጊዜያዊ አመራራቸውን አባላት ስም ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሲገልፁ የፓርቲው ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ተመስገን ዘውዴ መሆናቸውን እንደተረዱ የገለፁት እነዚሁ የፓርላማ አባላት በአዲሱ ፓርቲ ውስጥ የእነ ኢንጅነር ኃይሉና የሌሎችም የአመራር አባላት የኃላፊነት ቦታዎች እንደተጠበቁ ተደርጐ ለአንዳንድ ጋዜጦች የተገለፀበት ሁኔታ የቅንጅትን ሊቀመንበር ሥልጣን ያለጠቅላላ ጉባዔ ፈቃድና ውሳኔ ለመንጠቅ የተደረገ ሴራ መሆኑን እንደሚያመላክት ገልፀዋል፡፡ እነ ወ/ሪት ብርቱካን ያቋቋሙት "አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ" ፓርቲም ከቀድሞ የቅንጅት ፓርቲ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው አመልክተዋል፡፡

"[የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት] አዲስ የፈጠሩትን ፓርቲ የፊርማና ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የፓርቲዎችን መሪ ኢንጅነር ኃይሉ ናቸው በሚል ሽፋን መሆኑን ከደረሱን መረጃዎች ተገንዝበናል" ያለው የፓርላማ አባላቱ መግለጫ የቅንጅት አባልና ደጋፊዎች ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ መስራቾች ጐን እንዳይሰለፍ ጠይቋል፡፡

የፓርላማ አባላቱ ባቀረቧቸው ወቀሳዎች ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ፓርቲያቸው አላስፈላጊ እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት እንደማይፈልግ በመጠቆም ለቀረቡባቸው ውንጀላዎች ምላሽ መስጠት እንደማይፈልጉ ገልፀውልናል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >