Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ...
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ... Print E-mail
Sunday, 23 March 2008
Image
ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ያቀረበውን ጥያቄ ምርጫ ቦርድ አልተቀበለውም


የአንድነትና ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለምርጫ ቦርድ ያቀረበው የድጋፍ ደብዳቤ ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ ፓርቲው ያቀረበውን የድጋፍ ደብዳቤ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት መጋቢት 12 ቀን 2000 ዓ.ም ቀጠሮ በሰጠው መሠረት ያለፈው አርብ "የድጋፍ ደብዳቤ ምርጫ ቦርድ የመስጠት ህጋዊ ግዴታ የለውም" የሚል መልስ መስጠቱ ታውቋል፡፡

ወ/ት ብርቱካን ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ህጋዊ እውቅና እንዲያገኝ ከማደረግ አኳያ የአንድ ሺህ አምስት መቶ የመስራች አባላት ፊርማ ማሰባሰብ አንድ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ጠቅሰው፤ "ምርጫ ቦርድ የድጋፍ ደብዳቤ እንዲፅፍልን ያቀረብነው ጥያቄን አልተቀበለውም" ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት በርካታ ፓርቲዎች ሲቋቋሙ ጉዳዩ ወደ ቦርድ ሳይቀርብ በጽ/ቤት ደረጃ የፊርማ ማሰባሰቢያ የትብብር ደብዳቤ ይሰጥ እንደነበር ያወሱት ወ/ሪት ብርቱካን፣ "ይህ ልማድ ለምን እኛ ላይ ተቀየረ" የሚል ጥያቄ ለቦርዱ ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡ ቦርዱም ቀደም ሲል የነበረው ልማድ ትክክለኛ አለመሆኑንና ህገዊ መነሻም የሌለው መሆኑን መግለፁን አስታውቀዋል፡፡

ከቦርዱ ያለድጋፍ ደብዳቤ የፊርማ ማሰባሰብ ሂደት መቀጠል የሚችሉ መሆኑን እንደተገለፀላቸው ያሳወቁት ወ/ሪት ብርቱካን "በዚህም መሠረት የፊርማ ማሰባሰቡን ሂደት እንቀጥላለን" ብለዋል፡፡

ከፊርማ ማሰባሰቡ ሂደት በኋላ በመስራች አባላቱ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄዶ የአመራር አካላት እንደሚመረጥና የፓርቲውን ፕሮግራምና ደንብ በመስራች ጽሑፉ እንደሚዘጋጅም አስታውቀዋል፡፡ የመስራች ጽሑፉ ከፓርቲው ስያሜ ጋር ለምርጫ ቦርድ በማቅረብ የህጋዊ እውቅና ጥያቄ እንደሚቀርብ ወ/ት ብርቱካን አብራርተዋል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ምርጫ ቦርድን በስልክ ለማነጋገር ሞክረን "ከቢሮ ወጥተዋል" የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል፡፡

በተሾመ ንቁ
 
< Prev   Next >