| የተነሳው ቫት እና ተርን ኦቨር ታክስ... |
|
|
| Sunday, 23 March 2008 | |
|
የተነሳው ቫት እና ተርን ኦቨር ታክስ ሆቴሎችንና የፋብሪካ ውጤቶችን አይመለከትም
መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማርገብ ከመጋቢት 10 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ እንዲነሳ የወሰነው የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና ተርን ኦቨር ታክስ ሆቴሎችንና የፋብሪካ ውጤቶችን (የስንዴ ዱቄት በስተቀር) እንደማይመለከት ይፋ ሆነ፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሕዝብ ግንኙነት ማብራሪያ ጠይቀን በተሰጠው ምላሽ መሰረት ቫት እና ተርን ኦቨር ታክስ ነጻ የተደረጉት ምርቶች ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጥራጥሬ፣ የስንዴ ዱቄት እና የመሳሰሉት ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህ ውጪ የምግብ ዘይት፣ ስኳር እንዲሁም ሆቴሎች በቀድሞ አሰራር አንደሚቀጥሉ ተጠቅሷል፡፡ አንዳንድ ወገኖች የሚኒስቴሩ መግለጫ ላይ "የመሣሠሉት. . ". በሚል የተጠቀሰው ነገር ለተለያየ ትርጉም ክፍት በመሆኑ አደናጋሪ ሁኔታን እንደፈጠረ ለሪፖርተር ጋዜጣ አረጋግጠዋል፡፡ አንዳንድ የሆቴል ባለቤቶችም አንዳንድ ደንበኞቻቸው "መንግሥት ምግብ ላይ ቫት አንስቷል" በሚል ላለመክፈል ማንገራገራቸውን በመጥቀስ መመሪያው ግልጽ አይደለም የሚል ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |