Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ብሔራዊ ባንክ የ158 ሚሊዮን ብር...
ብሔራዊ ባንክ የ158 ሚሊዮን ብር... Print E-mail
Sunday, 23 March 2008
ብሔራዊ ባንክ የ158 ሚሊዮን ብር ወርቅ መጭበርበሩ ተረጋገጠ

ብሔራዊ ባንክ የ158 ሚሊዮን ብር ወርቅ እንደተጭበረበረ መረጋገጡን የፌዴራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አሰፋ አስታወቁ፡፡

አቶ ብርሃኑ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት ባንኩ ወርቅ በሚል ቅብ ብረትና የእህል ሚዛን ኪሎዎች በሳጥን እየታሸጉ ሲቀርብለት ግዢ ይፈፅም ነበር፡፡ እ.ኤ.አ 2005 እስከ 2007 ባንኩ ከወቅቱ ገበያ 158 ሚሊዮን ብር ተጭበርብሯል፡፡

መስከረም 29 ቀን 1995 ዓ.ም. በህገወጥ መንገድ ወደ ዱባይ ሊወጣ ሲል የተያዘው 38 ኪሎ ግራም ወርቅ ምርመራ እንዳልተጠናቀቀ ያስረዱት አቶ ብርሃኑ በወቅቱ ገበያ ባንኩ የተጠቀሰውን መጠን ብር መዘረፉ ያመለከቱት አቶ ብርሃኑ በወርቅ ማጭበርበር ዙሪያ የፌደራል ዋናው ኦዲተር 16 ገጽ የምርመራ (የኦዲት) ሪፖርት ለኮሚሽኑ ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡

ምርመራው ከሦስት ወር በላይ የቆየበትን ምክንያት ለተጠየቁት "ምርመራው ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋ በመሄዱ ሳቢያ ነው" በማለት አቶ ብርሃኑ መልስ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም "ሦስት ወር ተኩል የፈጀው ምርመራ እነማን፣ እንዴት፣ ከማን ጋር አጭበረበሩ የሚለውንና እነማን ይጠየቁ የሚለውን የወንጀል ሰንሰለት ሲመረመር ነው" ብለዋል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ታህሳስ 1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የጀመረው ምርመራ የሙስና ወንጀል በመሆኑ የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ህዳር 24 ቀን 2000 ዓ.ም. ወንጀሉን በማጣራት ሂደት ጉዳዩን በበላይነት መያዙ አይዘነጋም፡፡

በተጠርጣሪዎች ላይ የተወረሰውን ንብረት በተመለከተ ከተዘረፈው ሀብት ጋር ሲመጣጠን ከፍተኛ ሊባል የሚችል የንብረት ማስመለስ ሥራ መሰራቱን አቶ ብርሃኑ አመልክተዋል፡፡

በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብና ወርቅ በፍተሻ መያዙን የጠቆሙት አቶ ብርሃኑ የታገዱት የተጠርጣሪዎች ንብረትና የንግድ ድርጅቶች ሲደመሩ የተዘረፈውን የመንግሥት ሀብት ከማስመለስ አንፃር ከፍተኛ ሥራ ተሰርቷል ሊባል እንደሚችል አብራርተዋል፡፡

ወደ ዱባይ ሲወጣ የተያዘው ወርቅ ምርመራ እንዳልተጠናቀቀ ያስረዱት አቶ ብርሃኑ በቀረው ከወርቅ ጋር ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ኮሚሽኑ ምርመራውን ማጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ከወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በብሔራዊ ባንክ ሰባት፣ ከጆኦሎጂካል ሰርቬይ ላቦራቶሪ አራት፣ ከነጋዴዎችና ተባብረዋል በሚል የተጠረጠሩ አሥራ አምስት በድምሩ 26 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >