| ፌደራል ሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴርና... |
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
ፌደራል ሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴርና ሲጂሲ ቻይና የ2000 ገልባጭ መኪናዎች ግዢ ስምምነት ተፈራረሙ የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴርን በመወከል የተገጣጣሚ ህንፃ አካላት ማምረቻ ድርጅትና ሲጂሲ ኦቨር ሲስ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ሊሚትድ ከተባለ የቻይና ካምፖኒ ጋር የ2000 ገልባጭ መኪናዎች ግዢ ከትናንት በስቲያ ታህሳስ 25 2000 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡ የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ካሱ ኢላላ በስምምነቱ ወቅት እንደተናገሩት፣ መንግስት ከ400ሺ የማያንሱ የመኖሪያ ቤቶች /በኮንዶሚኒየም አይነት/ በአራት ዓመት ውስጥ ለመገንባት በያዘው ዕቅድ ለሲሚንቶ፣ አርማታ ብረትና የመፀዳጃ ዕቃዎችን በፍጥነት ለማጓጓዝ በማቀድ የግዥ ስምምነቱን እንደተፈራረመ ተናግረዋል፡፡ ለፕሮግራሙ ስኬታማነት መንግስት ቅድሚያ በመስጠቱ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሲሚንቶ፣ ከ150ሺ የማያንስ የአርማታ ብረትና ቀሪውን የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች በውጭ ምንዛሪ በመግዛት ላይ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ በአንድ ጊዜ 40 ቶን እንደሚጭኑ የተነገረላቸው ተሽከርካሪዎች የሌሎች የንግድ እንቅስቃሴ ሳይጎዳ ለቤቶች ልማት ፕሮግራሙ የሚያገለግሉ የግል ትራንስፖርት ባለንብረቶች በባለቤትነት እንዲገዟቸውና የቀረቡላቸውን እቃዎች ባስተማማኝ እንዲያጓጉዙ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ዶ/ር ካሱ ገልፀዋል፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴርን በመወከል የተገጣጣሚ ህንፃ አካላት ማምረቻ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ተሾመና የቻይና አምባሳደር ሚስተር ሊንሊን ሲሆኑ ሚኒስትሮችና አምባሳደሮችም ተገኝተዋል፡፡ በታምሩ ጽጌ |
|
| Last Updated ( Wednesday, 09 January 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |