| ለኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ስልጠና ሊሰጥ ነው |
|
|
| Sunday, 23 March 2008 | |
|
የዓለም የንግድ ድርጅት ለኢትዮጵያን ተደራዳሪዎችና የንግድ ባለሙያዎች አባልነቱ ለታደጊና ላላደጉ አገራት የሚኖረውን ጠቀሜታ በሚመለከት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ስልጠና ሊካሄድ ነው፡፡
ስልጠናው ከመጋቢት 22 ቀን እስከ 26 2000 ዓ.ም በሲዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚካሄድ ሲሆን የወርክሾፑ አላማ ኢትዮጵያ ለዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ የቡድኑ ስለሚያደርገው ሂደት ማሳወቅ ነው፡፡ ስምምነቱ ለማድረግ ስለሚያግዙ ስትራቴጂዎች፣ ትኩረት በሚሰጣቸው ዘርፎች ዙሪያ ውይይት ይካሄዳል የስልጠናው ተሳታፊዎች በግብርናና በአገልግሎት ዘርፍ ስለሚካሄዱ ስምምነቶችና በንግድ ሂደት አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችን እንዲያውቁ ያስችላል፡፡ በአገልግሎት ዘርፍ ለመደራደር የሚያስችል አቅም እንዲያዳብሩ እንደሚያስችላቸውም ተገል"ል፡፡ ስልጠናው ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት መስፈርቶችን እንድታሟላና በብሔራዊ ደረጃ አስፈላጊ የሆኑ የልማት አማራጮችን እንድታይ እገዛ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |