Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የታክሶቹ መነሳት በገጠር ያለውን....
የታክሶቹ መነሳት በገጠር ያለውን.... Print E-mail
Sunday, 23 March 2008
የታክሶቹ መነሳት በገጠር ያለውን የዋጋ ንረት በአጭር ጊዜ አያረጋጋም

በምግብ እህሎች ላይ የነበረው የተርን ኦቨርና የተጨማሪ እሴት ታክስ መነሳት በገጠር አካባቢ ያለውንና በምግብ እህሎች ላይ ያለውን የዋጋ ጭማሪ በአጭር ጊዜ መቀነስ እንደማያስችል ተጠቆመ፡፡ ሆኖም በከተማ የሚገኙ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች የማገዝ አቅም አለው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መጋቢት 9 ቀን 2000 ዓ.ም ለፓርላማ ባቀረቡት የ6 ወራት ሪፖርት እንደገለፁት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት በምግብ እህሎች ላይ ይጣል የነበረው የተርን ኦቨርና የተጨማሪ እሴት ታክስ መነሳቱ በዋጋ ንረቱ ላይ አሉታዊ ለውጥ ይኖረዋል፡፡ ሆኖም ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ የኢኮኖሚ ባለሙያ እንደሚሉት አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ገጠር አካባቢ ስለሚኖርና አብዛኛዎቹ ሸማቾችም አምራቾችም በመሆናቸው የዋጋ ንረቱን በአጭር ጊዜ የመቀነስ አቅሙ አናሳ ነው፡፡

የኢኮኖሚ ባለሙያው እንደገለፁት የታክሱ መነሳት በከተማ የሚገኙ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ቢያግዝም በዋጋ ንረቱ ተጨባጭና የሚታይ ለውጥ የማምጣት አቅሙ አናሳ ነው፡፡ የታክሱን መነሳት ተግባራዊ ለማድረግ ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል ከተደረገ በጥቂት ወራት ለውጥ ማምጣት አቅም ቢኖረውም ይህን ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችለው አቅም አናሳ ነው፡፡

በሌላ በኩል ታክስ፣ ድጓማና እርዳታ ጊዜያዊ የሆኑ የዋጋ ለውጦችን እንደሚያስተካክሉና ቀጣይነት ያላቸውን የዋጋ ንረቶችን ለማስተካከል የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት ያደረገ የፖሊሲ እርምጃ እንደሚያስፈልግ የአለም የገንዘብ ድርጅት አስታውቋል፡፡

አለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት የምግብ እህሎች ዋጋ መጨመርንና የነዳጅ ዋጋን ተከትሎ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገራት አዲስ የፖሊሲ አቅጣጫ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ጊዜያዊ የሆኑ የዋጋ ለውጦችን ለማስተካከል ጊዜያዊና የተወሰኑ ምርቶችን ታሳቢ ያደረገ ድጓማ፣ ታክስና እርዳታ ለውጥ የማምጣት አቅም እንዳላቸው ያስረዳል፡፡ ቀጣይነት ያላቸው የዋጋ ለውጦችን ለማስተካከል የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት ያደረገና በተወሰነ ጊዜ የዋጋ ንረቱን ለመግታት አቅም ያለው የፖሊሲ እርምጃ አስፈላጊ መሆኑ ተገል"ል፡፡

የሚወሰዱት የፖሊሲ አቅጣጫዎች በምግብ ምርቶች ላይ ያለውን የዋጋ ንረት ቀጣይ እንዳይሆን የሚያግዙ መሆን ሲኖርባቸው የገንዘብ ፖሊሲ እርምጃዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ የማምጣት አቅም እንዳላቸውም መረጃው ያስረዳል፡፡

ከነዳጅ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞም የመጣ ጊዜያዊም ሆነ ዘለቄታዊ የሆነ የምግብ እህሎች ዋጋ ጭማሪን ለማስተካከል የአገሪቱን ሁኔታ መሠረት ያደረገ የፖሊሲ ምላሽ እንደሚያስፈልግ ከድርጅቱ የወጣው መግለጫ ያስረዳል፡፡ የዋጋ ንረቱን ትክክለኛ ምክንያት ማወቅ የሚወሰዱ እርምጃዎች የተሻለ ለውጥ እንዲያመጡ ያስችላል፡፡ የዋጋ ንረት መንስኤው ጊዜያዊ ከሆነ የምግብ እህል ጭማሪዎች ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ እርምጃ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሆኖም የገንዘብ ፖሊሲው ተቀባይነት ካለውና አስተማማኝ ከሆነ እንዲሁም የዋጋ ንረቱ ቀጣይነት ከተረጋገጠ ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ምርቶች ላይ ጫና ከማሳደሩ በፊት እርምጃውን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

የምግብ እህል ዋጋ መጨመር በአለም ላይ በጨመረው የምግብ እህሎች ፍላጎት፣ የምርት መቀነስና ከእፅዋት ምርቶች የሚመረት ነዳጅ (ባዮ ፊውል) ፍላጎት ጋር ተያይዞ የመጣ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ለውጥ የማምጣት እድሉ አናሳ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

በግሎባላይዜሽን ሂደት በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተጎዱ በመሆኑ በየጊዜው የሚጨምረው የምግብ ምርቶች ዋጋ የእለት ምግባቸውን ማሟላት የማይችሉ ሰዎችን ቁጥር ያባብሰዋል፡፡ ለዚህም አቅም ያላቸው ተቋማት አዳዲስ መዋቀራዊ ለውጥ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

የምግብ እህሎች ዋጋ መጨመር በኢትዮጵያ በምግብ እህል ራሳቸውን ባለመቻላቸው በየአመቱ እርዳታ የሚጠብቁ ሰዎችን ቁጥር እንደሚጨምረውም ተገል ል፡፡
 
< Prev   Next >