| ሕንድና ኢትዮጵያ በቆዳ ኢንዱስትሪ... |
|
|
| Sunday, 23 March 2008 | |
|
ሕንድና ኢትዮጵያ በቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
ኢትዮጵያና ሕንድ በቆዳ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ገበያን በማፈላለግ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነደ ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን ባለፈው አርብ መጋቢት 12 ቀን 2000 ዓ.ም በተፈራረሙበት ወቅት ኢትዮጵያ በቆዳ ኢንዱስትሪው ካላት ሰፊ አቅም የሕንድ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች የሚሠሩበትን እድል፣ ፋብሪካዎችን በማቋቋምና ስልጠና በመስጠት እንደምታግዝ ተገል"ል፡፡ ሕንድ በበኩሏ አዳዲስ የቆዳ ምርት ገበያዎችን በማፈላለግና አዳዲስ ምርቶችን ለማምረት በሚያስችል የአቅም ግንባታ ፕሮግራም በምርምር ተቋም ግንባታና በሰው ኃይል ስልጠና እገዛ እንደሚታደግ የሕንድና አፍሪካ አጋርነት ስብሰባ ላይ የሕንድ የኮሜርስ ሴክሬተሩ ሚ/ር ጄኬ ፒላይ ግልፀዋል፡፡ አያይዘውም በቆዳ ዘርፍ ከአፍሪካ አገሮች የተሻለ አቅም ያለው በኢትዮጵያ ስለሆነ ስምምነቱን መፈራረማቸው በጋራ የሚሠሩበትን ሂደት ይፈጥራል ብለዋል፡፡ ታዳጊ አገሮች እርስ በእርሳቸው የሚወዳደሩበት መንገድ እንደሌለና ከበለፀጉ አገሮች ጋር በጋራ በመስራት ካላቸወን ሃብት የተሻለ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም የተናገሩት ሚ/ረ ፒላይ ፡፡ በቆዳው ሴክተር ካለው ሰፊ አቅም ለመጠቀም ለአቅም ግንባታ ፕሮግራም የሚውል የገንዘብና የስልጠና ተቋማትን በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለማስፋፋት ህንድ ዝግጁ መሆንዋንም አስታውቀዋል፡፡ የስልጠና ማዕከሉን በሚመለከት በምን ዓይነት መንገድ መገንባት እንደሚገባ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር የምርምር ፕሮግራሞችን እንደሚለዋወጡም አስታውቀዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |