Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 11th
Home arrow Sections arrow የኦባማን ፋይል የፈተሹ..
የኦባማን ፋይል የፈተሹ.. Print E-mail
Sunday, 23 March 2008
የኦባማን ፋይል የፈተሹ ተባረሩ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለኘሬዚዳንትነት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑትንና በሚስጢር የሚያዘውን የኦባማን የፓስፖርት ፋይል ሲመለከቱ ተደርሶባቸዋል ያላቸውን ሁለት ኮንትራት ሰራተኞች አባረረ፡፡

 

የመሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ማክ ከርማክ ድርጊቱን አምነው ሠራተኞቹ ምን እንዳዩ ወይም ምን ለማግኘት ፈልገው እንደነበር ለጊዜው ግልፅ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
የኦባማ ቃል አቀባይ በበኩላቸው መንግሥት የግለሰቦችን መረጃ ለፖለቲካ ጉዳይ ሊጠቀምበት ይችላል ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡

የቢቢሲ የሰሜን አሜሪካ ኤዲተር በፀጥታ ሰራተኞች ቀን ከሌሊት የሚጠበቀው ተወዳዳሪና የግለሰቦችን ፋይል ለማየት የሚያስችላቸውን ይለፍ የኮንትራት ሰራተኞች ማግኘታቸው ያልተለመደ መሆኑን ገልጿል፡፡ የኦባማ ቃልአቀባይ ጉዳዩ ቀጣይ ምርመራ እንዲደረግበት አሳስበዋል፡፡

*                          *                    *
የሂላሪ ክሊንተን የዕለት ማስታወሻ ሊታተም ነው
ሂላሪ ክሊንተን በኋይት ሃውስ የኘሬዚዳንት ሚስት ሆነው የቆዩበትን የስምንት ዓመት ጊዜ የሚገልፅ 11"000 ገፃችን ያሉት የዕለት ማስታወሻ ሊታተም ነው፡፡

ማስታወሻው የሚሰራጨው በአሜሪካ ብሔራዊ መዝገብ ቤት በኩል ሲሆን ማስታወሻውን እንዲታተም ግፊት የመጣው የመረጃ ማግኘት ነፃነት ቡድን ነው፡፡ የሂላሪ የዕለት ማስታወሻ ቶሎ እንዳይታተም ያጓትታሉ ሲሉ ተፎካካሪዎቻቸው ሲተቹ ቆይተዋል፡፡

ኦባማና የምርጫ አስተባባሪዎች የማስታወሻውን በፍጥነት መታተም ከሚፈልጉት ውስጥ ሲሆኑ መነሻቸውም ሂላሪ በባላቸው የኘሬዚዳንትነት ወቅት ያካበቱትን ልምድ እየጠቀሱ ስለሚናገሩ ያንን ለማረጋገጥ ነው፡፡

በተለይ የአሜሪካ የጦር ኃይል አዛዥ ለመሆን ያላቸው ልምድ ምን እንደሆነ ከማሰታወሻው ለማየት ፈልገዋል፡፡

በማስታወሻው ላይ የቀድሞው ኘሬዚዳንት ለሚመሰገኑበት የአየርላንድና የኮሳቮ ችግር በመፍታት ድርሻ እንደነበራቸው ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡

*                          *                    *
የሙጋቤ ተቀናቃኞች የድምፅ አቆጣጠሩን ተቃወሙ

የዙምባብዌ ተቀዋሚ መሪ የኘሬዚዳንታዊ ምርጫ ቆጠራ በማዕከላዊ ጣቢያ ሊካሄድ መታቀዱን እንደሚቃወሙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡  መሪው ሞርጋን ሳቫንጊራይ "ይህ ማዕከላዊ የድምፅ ቆጠራ ምርጫው እንዲጭበረበር መንገድ ይከፍታል፡፡ የዚህ ሕገወጥ ሂደት አካል አልሆንም" በማለት ድምፆች በየምርጫ ጣቢያዎች መቆጠር እንደሚኖርባቸው አመልክተዋል፡፡ የመራጮች መዝገብ ላይም በሺህ የሚቆጠሩ የሀሰት ስሞች እንደነበሩም ጠቁመዋል፡፡

የኘሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ የምርጫ ሕግን መቀየር ተከትሎ በሚስተር ሳቫንጋራይ የሚመራው ሙቭመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ወደ ፍርድ ቤት ቢሄድም ምርጫው ሊጭበረበር ይችላል የሚለውን የተቃዋሚዎች አቤቱታ የሮበርት ሙጋቤ መንግሥት ውድቅ አድርጐታል፡፡

*                          *                    *
የፍልስጤም አንጃዎች ውይይት ተቋረጠ
በሁለቱ የፍልስጤም ተቀናቃኝ አንጃዎች ፋታህና ሀማስ መካከል እየተደረገ የነበረው ድርድር መቋረጡን የፋታህ መሪ ሞሀመድ አባሳን በመጥቀስ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡  በየመን ሰንአ እየተካሄደ ለነበረው ስምምነት መቋረጥ ሁለቱም ወገኖች እርስ በርስ ተወነጃጅለዋል፡፡

ጋዛ በብሔራዊ አንድነት መንግሥት ቁጥጥር ሥር መዋል እንዳለበትና አዲስ ምርጫም እንዲካሄድ አደራዳሪዎች ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ሁለቱም ወገኖች የሚያደርጉት ውዝግብ ፍልስጤም ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ቢያምኑም መግባባት ላይ ግን ሊደርሱ አለመቻላቸውን ዘገባው ያመለክታል፡፡

የአለመግባባቱ ዋነኛ ነጥብ የሆነው ሀማስ 2007 ላይ በኃይል የያዘውን የጋዛ ግዛት ይልቀቅ የሚለው የፋታህ ጥያቄ ነው፡፡ ሀማስ በበኩሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይህንን እንደማያደርግ አሳውቋል፡፡

*                          *                    *

 
< Prev   Next >