Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ዕድሮች የሸማቾች ሕብረት ሥራ...
ዕድሮች የሸማቾች ሕብረት ሥራ... Print E-mail
Sunday, 23 March 2008
ዕድሮች የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበር ለማቋቋም እየተንቀሳቀሱ ነው

በአዲስ አበባ አስተዳደር በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ ዕድሮች የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበር ለማቋቋም የሚያስችላቸውን እንቅስቃሴ በማከናወን ላይ መሆናቸውን አቶ መለሰ ተካ የአዲስ አበባ ዕድሮች ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ገለፁ፡፡

እስካሁንም ባካሄዱት እንቅስቃሴ የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበርን አስመልክቶ ለዕድር አባላቱ የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት በመስጠትና አስፈላጊውን ቅስቀሳ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ምክትል ሊቀመንበሩ አስረድተዋል፡፡

የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበር በሚቋቋምበት ጊዜ በአቅም ውስንነት ሳቢያ አክሲዮን መግዛት ለማይችሉ የዕድሩ አባላት የየዕድሩ ምክር ቤቶች በስማቸው የአክሲዮን ዕጣ እንደሚገዙላቸውና አባላቱም በረጅም ጊዜ ክፍያ ዕዳቸውን ለመሸፈን የሚያስችላቸው ሁኔታ እንደሚመቻችላቸው አቶ መለሰ አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በየቀበሌውና በአስሩም ክፍለ ከተሞች የዕድሮች ምክር ቤቶች መቋቋማቸውን አቶ መለስ አመልክተው የክፍለ ከተሞቹ ዕድር ምክር ቤቶች ደግሞ በአዲስ አበባ አስተዳደር የጋራ መድረክ መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡

እነዚሁ ምክር ቤቶችም በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የደም ልገሳ እንዲካሄድ በማድረግ፣ በኤች አይ ቪ/ኤድስና በሌላም ሳቢያ ወላጅ አልባ የሆኑ ሕፃናትን በመንከባከብና በአጠቃላይ በኤች አይ ቪ ዙሪያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ትምህርት በመስጠት የሚደነቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ኃላፊው አመላክተዋል፡፡
 
< Prev   Next >