|
Sunday, 23 March 2008 |
|
በአርብቶ አደር ወረዳዎች የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳያደርሰ ተፈርቷል
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ዘጠኝ የአርብቶ አደር ወረዳዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአርብት አደር ቋሚ ኮሚቴ አባላት አሳሰቡ፡፡
የልኡካን ቡድኑ በቦረና የተለያዩ ወረዳዎች ተዘዋውሮ ወቅታዊ ሁኔታውን በተመለከተበት ወቅት በዞኑ ባለው የዝናብ እጥረት ምክንያት በርካታ የአርብቶ አደሩ እንስሳት ለምግብና ውሀ እጦት ተዳርገዋል፡፡ ችግሩ በተከሰተባቸው ወረዳዎች በድሬ፣ ያቤሎ፣ ሞያሌና ዳአስ ወረዳዎች ተዘዋውረው እንደተመለከቱት ከፍተኛ የውሀና የመኖ እጥረት በመከሰቱ ምክንያት አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አርብቶ አደሮችን በማነጋገር ለመረዳት መቻሉን ገልፀዋል፡፡
* * * ከነገ ጀምሮ የገብስና የማሽላ ምርቶችን ከአገር ውጭ መላክ አይቻልም
ከመጋቢት 15 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ የገብስና የማሽላ ምርቶችን ከአገር ውጭ መላክ እንደማይቻል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በከተማዋ የሚታየውን የምግብ እህል ዋጋን ለማረጋጋት መንግሥት በወሰደው እርምጃ ከተከለከሉት እህሎች በተጨማሪ ገብስና ማሽላም ወደ ውጭ እንዳይላኩ እገዳ ተጥሏል፡፡ እነዚሁ ምርቶች የተከለከሉት በተወሰነ ደረጃ የምግብ አቅርቦትን ለማመቻቸትና በሌሎች ምርቶች ላይ የታየውን የዋጋ ንረት ከማረጋጋት አንጻር አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ በመታመኑ መሆኑን፣ ከዚህ በፊት ወደ ውጭ እንዳይላኩ በተከለከሉትም ሆነ የገብስና ማሽላ ምርቶችን በተፈጨም ሆነ በጥሬ መልኩ ወደ ውጭ መላክ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ይሁን እንጂ አንዳንድ ሕገወጦች አስድሞ የተከለከሉትን ምርቶች ከአገር ውስጥ ለማስወጣት እንደሚሞክሩ የተስተዋለ በመሆኑ በነጋዴዎች ላይም እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡ ይህን መሰሉ ተግባርም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድቷል፡፡
* * * አንዲት ግለሰብ 3 ሺህ ብር በጭልፊት አሞራ ተነጠቁ
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሂርና ከተማ ውስጥ አንዲት ግለሰብ 3 ሺህ ብር በጭልፊት አሞራ መነጠቃቸውን የዞኑ ፖሊስ ገለጸ፡፡
ግለሰቧ በጭልፊት አሞራ የተነጠቁት ከሂርና ንግድ ባንክ ያወጡትን ገንዘብ በፌስታል ጠቅልለው በእጃቸው እንደያዙ ነው፡፡
የአካባቢው ሕዝብ ገንዘቡን ከጭልፊት አሞራ ለማስጣል ቢሞክርም ጭልፊት አሞራው በአካባቢው ለተለወሰነ ጊዜ ካንዣበበ በኋላ ከአይን በመሰወሩ ሊያስጥሉት እንዳልቻሉ ተናግረዋል፡፡
ገንዘቡን የተነጠቁት ግለሰብ በበርበሬ ንግድ ሥራ የሚተዳደሩ ሲሆን በወቅቱ ከፍተኛ መደናገጥ ይታይባቸው እንደነበርም ገል..ል፡፡
* * *
የብሔራዊ የቡና ሙዚየም ግንባታ ዲዛይን ለውይይት ቀረበ
በደቡብ ክልል በከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ የሚገነባው ብሔራዊ የቡና ሙዚየም ግንባታ የመጀመሪያ ምእራፍ ዲዛይን ለውይይት ቀረበ፡፡ በብሔራዊ ሚሌኒየም በዓል አከባበር በምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባለድርሻ አካላት ዲዛይኑ ለውይይት በቀረበበት ወቅት ዲዛይኑ የአካባቢውን ተፈጥሮአዊና የህብረተሰቡን የአኗኗር ባህላዊ እሴቶች ያገናዘበ መሆኑን ገል..ል፡፡
የሙዚየሙ ዲዛይን በቦንጋ አባባቢ የሚገኙ ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ ቅርሶች ለቱሪስት እይታ የሚቀርቡበትን ሁኔታ ያገናዘበ እንደሆነ የሙዚየሙ መገንባት ሀገሪቱ አማራጭ የቱሪስት መስመሮች እንዲኖራት ከማድረጉም በላይ የገቢ ምንጮችን ለማሳደግና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋፋት እንደሚረዳ አስታውቀዋል፡፡
* * *
የዋጋ ንረትን አባብሰዋል የተባሉ አስር ነጋዴዎች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ በጎንደር ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ የተለያዩ የምግብ ፍጆታዎችን በመጋዘናቸው በመደበቅ የገበያ አለመረጋጋት ፈጥረዋል ተብለው ክስ የተመሰረተባቸው አስር ነጋዴዎች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ፡፡
የከተማዋ ንግድ ኢንዲስትሪና ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፤ በከተማዋ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ማድረጋቸው ተረናገግጦ ከታሸጉት 78 የንግድ ድርጅቶች መካከል የአስሩ ድርጅቶች ባለቤቶች በፍርድ ቤት በተመሰረተባቸው ክስ በእሥራትና በገንዘብ ተቀጥተዋል፡፡
የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ድርጅታቸው እንዲታሸግባቸው ከተደረጉት መካከል የንገድ ፍቃድ ሳያወጡ ሲሠሩ የተገኙና የኑሮ ውድነትን በማባባስ የከፋ ችግር መፍጠራቸው በማስረጃ የተረጋገጠባቸው አስር ነጋዴዎች በተመሠረተባቸው ክስ በአራት ወር እስራትና እስከ 6 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ መወሰኑን ገል..ል፡፡ |