| የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር በወጣው... |
|
|
| Sunday, 23 March 2008 | |
|
የቲቢ በሽታን ለመቆጣጠር በወጣው ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ክትትል እየተደረገበት ነው
ከመላ ሀገሪቱ በሚሌኒየሙ የቲቢ በሽታን ሥርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው የእቅድ አፈጻጸም ላይ ያተኰረ ክትትል በመካሄድ ላይ መሆኑን ዶክተር ዘሪሁን ታደሰ በጤና ጥበቃ ሚኒስትር የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ መምሪያ ኃላፊ አስታወቁ፡፡ ክትትሉን የሚያደርጉትም የፌዴራል ጤና ጥበቃ፣ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎችና በተዋረድ ያሉ ሌሎች ኃላፊዎች መሆናቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከፍተኛ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ኃላፊው አመልክተው ከተከናወኑትም ተግባራት መካከል ሕብረተሰቡ ስለ ቲቢ በሽታ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ማስቻል አንዱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ዘንድሮ የሚከበረውም የዓለም የቲቢ ቀን አከባበር ይህንን ዓለማ በሚያግዝ መልኩ እንዲሆን መታቀዱን፣ ዕለቱም በዓለም ደረጃ "አይ አም ስቶፒንግ ቲቢ" እና በአገር አቅፍ ደረጃ ደግሞ "የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ለቲቢ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ቁልፍ ሚና አላቸው፡፡" በሚል መርህ ሀሳብ የሚከበር መሆኑን ዶ/ር ዘሪሁን ተናግረዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |