Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ሁለተኛው አዲስ ዓለም...
ሁለተኛው አዲስ ዓለም... Print E-mail
Sunday, 23 March 2008
Imageሁለተኛው አዲስ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ተከፈተ

ሁለተኛው አዲስ አለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል በመብትና ፍትህ ላይ በማተኮር በኢኒሼቲቭ አፍሪካ አስተባባሪነት ለሁለተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ነው፡፡

 

ከመጋቢት 12 እስከ 21 የሚቆየውን የፌስቲቫሉን መክፈቻ አስመልክቶ ያለፈው አርብ በግሎባል ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣው መግለጫ ፌስቲቫሉ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተዘጋጁና ርዕሰ ጉዳያቸው በመብትና ፍትህ ላይ የሚያጠነጥኑ ምርጥ ፊልሞች ለህዝብ እይታ የሚቀርቡበት ይሆናል፡፡

በፌስቲቫሉ ተሸላሚ የሚሆነው የኢትዮጵያ ፊልም በአለም ደረጃ በሚካሄደው አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ለዕይታ ይቀርባል፡፡

ፌስቲቫሉ በመብትና ፍትህ ዙሪያ የሚያተኩሩ የአገር ውስጥና የውጭ ፊልሞችና ጥናታዊ ፊልሞችን በአንድ መድረክ እንደሚያገናኝ ተገልጿል፡፡ በፌስቲቫሉ የመብትና የፍትህ ጭብጥ ያላቸው በኢትዮጵያውያን የፊልም ባለሙያዎች የተዘጋጁና በፌስቲቫሉ ለውድድር የቀረቡ ፊልሞች በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው ዳኞች ታይተው በአንደኝነት የሚወጣው ፊልም የፌስቲቫሉ ተሸላሚ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት የኢንሼቲቭ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክቡር ገና "ሑቈሸሮቃሽቫሽቃሸ the በቃቄቈሸሮቃሽቫስሳ" በሚል መጠሪያ የዘንድሮው የፊልም ፌስቲቫል መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ፌስቲቫል የአገራችንን የፊልም ጥበብ በማሳደግ ደረጃ አስተዋጽኦ እንሚኖረውና የመብትና የፍትህ አስተሳሰብን በኅብረተሰቡ ዘንድ እንዲጎለብት ከማድረግ አንፃር ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

በፌስቲቫሉ መክፈቻ ላይ በኢትዮጵያ የቡና አምራቾች ህይወት ዙሪያ የተሰራው "ብላክ ጎልድ" የተሰኘው ፊልም ለእይታ ቀርቧል፡፡ በፊልሙ በመሪ ገፀ ባህሪይነት የተሳተፉት አቶ ታደሰ መስቀላ "ፊልሙ የቡና አምራች ገበሬዎች ህይወትን ከመቀየር አንፃር ሰፊ ሚና አበርክቷል" ብለዋል፡፡ አቶ ታደሰ ብላክ ጎልድ በመላው አለም ለዕይታ በመቅረብ ውዝግብ ያስነሳና የኢትዮጵያን የቡና አብቃይ ገበሬዎችን ህይወት በማንፀባረቅ ግንዛቤ እንደፈጠረ አስታውቀዋል፡፡

------------

 
< Prev   Next >