| ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን... |
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገው የጃክሮስ ካምፓኒ ተበዳዮች ነን የሚሉት ያቋቁሙት ..ሾላ አክሲዮን ማኅበር.. ከአዲስ አበባ አስተዳደር ሊዝ ጽ/ቤት በስማቸው የተረከበውን ቦታ ለ11ዱ አባላት እንዲያረክባቸው የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሻረው፡፡ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታህሳስ 18 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችሎቱ በአክሲዮን ማኅበሩ ይግባኝ ባይነት የተላለፈለትን ክስ የሻረው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ለማየት ሕጋዊ ስልጣን የለውም በማለት ነው፡፡ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘነው ማስረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 ቁጥር 41/1/ሀ/መሠረት፣ የከተማ መሪ ፕላን አፈፃፀም የሚመለከት፣ የይዞታ ባለመብትነት፣ የፈቃድ አሰጣጥ፣ ወይም የቦታ አጠቃቀምን በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮችን አይቶ የሚወስን የዳኝነት ስልጣን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት መሆኑን ይገልፃል፡፡ የፍርድ ቤትን ስልጣን በተመለከተ ከባለጉዳዮች ባይነሳም ፍርድ ቤት ራሱ በማናቸውም ጊዜ ሊያየው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ/ቁጥር 9 እንደሚያመለክት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሳኔ ማስረጃ ላይ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጃክሮስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ ከ205 በላይ ሰዎችን የመኖሪያ ቤት ለመስራት በሚል ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ ከሰበሰበ በኋላ ቤቶቹን ሳይሠራ መቅረቱንና በፍርድ ቤት እንዲከፍል መወሰኑን፣ 110 ሰዎች በመደራጀት ሾላ አክሲዮን ማኅበር የተባለ ማኅበር ማቋቋማቸውን፣ ማኅበሩን ሲያቋቁሙ 11 ሰዎች ሳይካተቱ በመቅረታቸው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርተው እንደተወሰነላቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በታምሩ ጽጌ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |