| በአዲስ አበባ በፈረቃ የኤሌክትሪክ... |
|
|
| Wednesday, 26 March 2008 | |
|
በአዲስ አበባ በፈረቃ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ አነጋጋሪ ሆኗል
ኮርፖሬሽኑ ጥገና እንጂ ፈረቃ አይደለም ይላል በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል በተደጋጋሚ እየተቋረጠ መሆኑን፣ ኮርፖሬሽኑ ለሕዝብ ይፋ ሳያደርግ የፈረቃ ኘሮግራም ሳይጀምር አይቀርም የሚል ግምት እንዳላቸው አንዳንድ ደንበኞቹ ሲያስታውቁ ኮርፖሬሽኑ የደንበኞቹን ቅሬታ አስተባብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ካለፈው አንድ ወር ወዲህ የኤሌክትሪክ ኃይል በፈረቃ እንደሚጠፋ ያስታወሱት አንዳንድ ተጠቃሚዎች በይፋ የተገለፀ ነገር ባለመስማታቸው ችግሩ ምን እንደሆነ ለማወቅ መቸገራቸውን ገልፀዋል፡፡ አቶ ሰንደቁ አርአያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ማብራሪያ “ኮርፖሬሽኑ ለሕዝብ ሳያስታውቅ የፈረቃ ኘሮግራም አልጀመረም” ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች የኤሌክትሪክ መስመሮች ያረጁ መሆናቸውን፣ እነሱንም ለመጠገን ቀጣይነት ያለው የጥገና መርሐ ግብር ዘርግቶ እየሠራ መሆኑን አስታውሰው ከዚህ ጋር በተያያዘ ከጠዋቱ 12፡ዐዐ ሰዓት እስከ 6፡ዐዐ ሰዓት፣ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡ዐዐ ሰዓት ብቻ ከ24 ሰዓታት አስቀድሞ ለኀብረተሰቡ በመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያ አስነግሮ ኃይል እንዲጠፋ ሲያደርግ መቆየቱን አረጋግጠዋል፡፡ አቶ ሰንደቁ አያይዘውም “ከምሽቱ 12፡ዐዐ ሰዓት በኋላ በድንገተኛ የቴክኒክ ችግር ካላጋጠመ በስተቀር መብራት ጨርሶ አይቋረጥም” ብለዋል፡፡ እንደ ሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጁ ገለፃ ከሆነ በምሽት ወቅት አንዳንድ ፋብሪካዎች ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚወስዱ፣ መጠነኛ ኃይል የሚቀነስባቸው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ከጥገና ጋር በተያያዘ የኃይል መቋረጡ እስከ መጪው ክረምት መግቢያ ድረስ እንደሚቀጥልም በማረጋገጥ ጉዳዩ ከፈረቃ አሠራር ጋር እንደማይገናኝ አስታውቀዋል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |