Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 25th
Home arrow Sections arrow የድሬዳዋን የወደፊት ራዕይ እንዲያሳይ...
የድሬዳዋን የወደፊት ራዕይ እንዲያሳይ... Print E-mail
Wednesday, 26 March 2008
የድሬዳዋን የወደፊት ራዕይ እንዲያሳይ የተሰራ ስዕል ውዝግብ ፈጠረ

የድሬዳዋ 105ኛ በዓል ሲከበር የከተማዋን የወደፊት ራዕይ ያሳያል ተብሎ የተሰራ ሥዕል በድሬዳዋ ሚሌኒየም ጽህፈት ቤትና የሥዕሉ ባለቤት ነኝ በሚሉት ግለሰብ መካከል ውዝግብ አስነሳ፡፡ ጽህፈት ቤቱ ምንም ዓይነት ስምምነት ስለሌለን የማውቀው ነገር የለም ይላል፡፡
 
በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 05 ነዋሪ የሆኑትና ለድሬዳዋ 105ኛ በዓል አከባበር ላይ የሚቀርብ፣ የድሬዳዋን የወደፊት ራዕይ የሚያሳይ የስዕል ውድድር በመኖሩ፣ በውድድሩ እንዲሳተፉ የተነግራቸው አቶ ግዛው ነገራ፣ በራሳቸው የሥዕል ፈጠራ በመስራትና የቀለም ጥንቅር (የከለር ሴፓሬሽን) ሥራውንም በመስራት አጠናቀው ህዳር 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ለሚሌኒየም ፅህፈት ቤት ማስረከባቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡

“የሠራሁት ሥራ አሸናፊ መሆኑና አለመሆኑ ካለመገለፁም በተጨማሪ ምንም ክፍያ ሳይከፈለኝ በበዓሉ ዕለት በከተማችን ሁለት መግቢያ በሮች ማለትም በኤርፖርትና በኃይስኩል መግቢያዎች ላይ ተሰቅሎ አየሁት” ብለዋል፡፡

የፈጠራ ሥራቸው የሆነውን ሥዕል ከሳቸው ፈቃድ ውጪ በድሬዳዋ መግቢያ በሮች ላይ ከመሰቀሉ በተጨማሪ፣ ሥራዎቻቸው በዲጂታል፣ በፖስተሮችና በጋዜጦች ላይ ወጥተው በማየታቸው፣ ያላቸውን የሥራ ሞራል እጅግ መጐዳቱን አቶ ግዛው ተናግረዋል፡፡

አቶ ግዛው ጨምረው እንደገለፁት፣ የሥዕልና የኪነጥበብ ችሎታ እንዳላቸው፣ በካላንደሮች፣ በትምህርት መፃህፍቶች፣ በማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ በቴሌቪዢንና ራዲዮ ሥራዎቻቸው እንዳቀረቡና አስፈላጊውም ክፍያ ሲፈፀምላቸው እንደነበር ገልፀዋል፡፡

“ለድሬዳዋ 1ዐ5ኛ በዓል እንድወዳደር ተጠይቄ ከተወዳደርኩ በኋላ ማሸነፌ ሳይገለፅና ተገቢው ዕውቅናና ክፍያ ሳይፈፀምልኝ በከተማዋ ዋናዋና በሮች ላይ የተሰቀሉትን የእምሮዬ ውጤቴን በተመለከተ የሚመለከተው አካል ሊታደገኝ ይገባል” በማለት አቶ ግዛው ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ሚሌኒየም ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አብዱላሂን ስለተፈጠረው አለመግባባት ጠይቀናቸው፣ “ፖስተሩ 1ዐ5ኛ በዓላችንን ለማስተዋወቅ በዕቅዳችን የተያዘ ነው፡፡ ይኸንን ተግባራዊ የሚያደርግ 12 አባላት ያሉት ኮሚቴም አቋቁመን ነበር፡፡ ከዘህ በኋላ የማውቀው ጉዳይ ስለሌለ የቅስቀሳና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑትን አቶ አብዱጀባል አቡበከርን ጠይቁ” ብለዋል፡፡

አቶ አብዱልጀባል አቡበከርን ጠይቀናቸው፣ ባለቤት ነኝ ከሚለው ግለሰብ ጋር ምንም ዓይነት ስምምነት እንደሌላቸው፣ ፅንሰ ሀሳቡ (Idia) የሌላ ሰው መሆኑን፣ ዲዛይኑን ሌላ ድርጅት እንደሰራውና በዓሉ ካለፈ በኋላ ግለሰቡ የእኔ ሥዕል ነው ብሎ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡

“ያለ ምንም ውል ምንም የሚፈፀም ነገር የለም” ያሉት አቶ አብዱልጀባል፣ “ውልም ባይኖር ምንም ችግር የለውም” በሚል፣ ከማኔጅመንቱ አራት ሰዎች በመሆን ፅህፈት ቤቱን አሳምነው፣ “ይኸ ልጅ ምንም ይሁን ምን፣ እዚህ ውስጥ ተሳትፎ አለው በሚል አንድ ሺ ብር እንዲሰጠው ተወሰነለት” ብለዋል፡፡

ልጁ የተወሰነለትን ብር አልወስድም ማለቱን፣ ለተወዳዳሪዎች ያዘጋጁት ምንም ሽልማት አለመኖሩን፣ በዚህም መሠረት ብዙ ሰዎች ለበዓሉ ብዙ ነገር በማድረጋቸው ምንም የተከፈለ እንደሌለ ገልፀዋል፡፡

“አንድ ጊዜ ስምምነት የለንም? ሌላ ጊዜ ይኸንን ያህል እንክፈልህ ብንለው እምቢ አለን? ሲሉ ሁለቱ አባባል አይጋጭም” ወይ? በሚል ጠይቀናቸው፣ “በዚህ ላይ ምላሽ የለኝም” ብለዋል፡፡

በታምሩ ጽጌ
 
< Prev   Next >