Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Tuesday
May 13th
Print E-mail
Wednesday, 26 March 2008
Imageየኦህዴድ 18ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ጋር በተያያዘ በትላንትናው ዕለት በአዳማ (ናዝሬት) የኦሮሞ ጀግኖች ሰማዕታት ሐውልት፣ የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ሕንፃ እና የራዲዮ ጣቢያ በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

ሐውልቱ ከጉልበት እስከ መቀመጫ ድረስ ያለውን አጥንት የሚያሳይ ሲሆን አጥንቱ ረዥም የሰውነት ክፍል የሚወክል፣ ረዥም ጊዜ መራራ ትግል መካሄዱን የሚያመለክት ነው፡፡ የሐውልቱ ጭንቅላት የተያያዘው አንድነትና አብሮ መቆምን ለማሳየት ታስቦ ነው ተብሏል፡፡

የሐውልቱ ግንባታ ብቻ 63.3 ሚሊየን ብር የፈጀ ሲሆን ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 23 ሚሊዮን ብር ያህሉን የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሆኑ የኦህዴድ የቀድሞ ታጋዮች የተዋጣ ሲሆን ቀሪው በሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ መሸፈኑ፣ ግንባታውንም ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ማከናወኑ ታውቋል፡፡

በምረቃው ሥነስርዓት ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስትርና የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር አቶ አዲሡ ለገሰን ጨምሮ የክልል ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
 
< Prev   Next >