| የቢሾፍቱ የታክሲ ባለንብረቶች... |
|
|
| Wednesday, 26 March 2008 | |
|
የቢሾፍቱ የታክሲ ባለንብረቶች አዲሱን ታሪፍ ተቃወሙ
በቢሾፍቱ ከተማ የሚሰሩ ታክሲዎች በትላንትና ዕለት አዲስ የወጣውን ታሪፍ በመቃወም ለግማሽ ቀን የሥራ ማቆም አደረጉ፡፡ የቢሾፍቱ ከተማ ታክሲዎች የሥራ ማቆም እንዲያደርጉ ምክንያት የሆናቸው በንግድና ኢንዱስትሪ እና በመንገድ ትራንስፖርት የወጣውን ታሪፍ በመቃወም ነው፡፡ ከትላንት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በከተማው አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የወጣው ታሪፍ በአጭር ርቀት ቀድሞ ዘጠና ሳንቲም (0.90) የነበረውን ሰባ አምስት (75) ሳንቲም እንዲሆን ወስኗል፡፡ ለረጅም ርቀት ቀድሞ የነበረው 1.20 ብር ሲሆን አሁን ከሦስት ቦታ በመቁረጥ በአጭር ርቀት ዋጋ እንዲከፍል ያዛል፡፡ ይኸም ዋጋውን 2.25 ብር ከፍ ያደርገዋል፡፡ በቀጥታ ለመሄድ ግን 1.30 ብር እንዲሆን በታሪፉ መግለጫ መደንገጉን የዜና አቀባያችን ከቢሾፍቱ ዘግቧል፡፡ የታክሲ ባለንብረቶቹ የአጭር ርቀቱ ተመኑ፣ ቀድሞ አስተዳደሩ ከወሰነው 90 ሳንቲም ወደ 75 ሳንቲም ዝቅ እንዲል መደረጉን ተቃውመዋል፡፡ "ቀድሞ ከነበረው ተመን አሁን የነዳጅ ዋጋ በጨመረበት ወቅት ለምን ዝቅ እንዳለ ሊገባን አልቻለም" ይላሉ አንድ የታክሲ ባለንብረት፡፡ የረጅም ርቀቱን መንገድ በሦስት ቦታ ከፍሎ በአጭር ርቀት መተመኑ ለሕብረተሰቡ ጫና የሚፈጥር በመሆኑ መቃቃርን ያመጣል የሚል ስጋት አላቸው፡፡ የሥራ ማቆም አድማው የተከናወነው በከተማዋ አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ደጃፍ ታክሲዎቹን በማቆም ነው፡፡ የዜና አቀባያችን ከቢሾፍቱ እንደዘገበው ከሆነ ቀትር ላይ የከተማዋ የአስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪና የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ባለንብረቶቹን አነጋግረው ስምንት ተወካዮች ብቻ እንደሚያነጋግሩና ሌሎቹ ሥራቸውን በአዲሱ ተመን እንዲያከናውኑ ተስማምተው ታክሲዎቹ ከሰዓት በኋላ ሥራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ከሰዓት በኋላ የባለታክሲዎቹን ስምንቱ ተወካዮች፣ አስተዳደሩ አነጋግሮ፣ መልሱን ለሐሙስ እንደሚያስታውቅ፣ እስከዚያው ታክሲዎች ስራቸውን እንዲቀጥሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የዜና አቀባያችን ከላከልን ዜና ለመረዳት ይቻላል፡፡ የባለታክሲዎቹን ጥያቄና ከአስተደደሩ የተወሰደውን ርምጃ አስመልክቶ የቢሾፍቱ አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ለማነጋገር ደጋግመን የስልክ ጥሪ ብናደርግም ስልኩ ሊነሳ ባለመቻሉ ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |