Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
May 09th
Home arrow Sections arrow ፖሊሲ ለዋጋ ንረት መፍትሄ
ፖሊሲ ለዋጋ ንረት መፍትሄ Print E-mail
Wednesday, 26 March 2008
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የኢኮኖሚ ቀውስ በሚያስከትለው ችግር የመጀመሪያ ተጠቂዎች ናቸው፡፡ በየወቅቱ እያሻቀበ የሚሄደው የምግብ ምርቶች ዋጋ በቀን ሦስት ጊዜ ቀርቶ አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ የሚሳናቸው ሰዎችን ቁጥር በእጥፍ እንዲያድግ ያደርገዋል፡፡

በሪፖርተር ጋዜጣ በመጋቢት 14 ቀን 2000 ቢዝነስና ኢኮኖሚ ገጽ "የታክሶች መነሳት በገጠር ያለውን የዋጋ ንረት በአጭር ጊዜ አያረጋጋም" በሚል ርዕስ የቀረበው ጽሑፍ ይህንኑ ይጠቁማል፡፡ ከዚህ በመነሳት የታክሶች መነሳት አፋጣኝና ተጨባጭ ለውጥ ያመጣል ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡

ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው በገጠሩ አካባቢ ነው፡፡ የዋጋ ንረቱን በአጭር ጊዜ የመቀነስ አዝማሚያ አይታይበትም፡፡ ንረቱ የዕርዳታ ፈላጊዎችን ቁጥር ከፍ እንደሚያደርገው ግልጽ ነው፡፡

ለዚህ ችግር መፍትሄው የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የፖሊሲ እርምጃ መውሰድ ነው፡፡ ይህ አይነቱ እርምጃ አማራጭ የሌለው መሆኑን የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት መግለጫ ያስረዳል፡፡ እንደ መግለጫው ከሆነ ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ አገሮች የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር አዲስ የፖሊሲ አቅጣጫ መንደፍ ይኖርባቸዋል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ የማምጣት ዕድሉ አናሳ ከሆነው ተርን ኦቨርና ተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ ከመዘናጋት ይልቅ ዘላቂ መፍትሄ ሊያስገኙ በሚችሉት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው፡፡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሴክተር መሥሪያ ቤቶች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በቅንጅት መንቀሳቀስ አለባቸው፡፡

(ሣምሶን ከበደ፣ ከልደታ)
 
< Prev   Next >