| የሱዳን መንግሥት የተመድን ሪፖርት አጣጣለ |
|
|
| Wednesday, 26 March 2008 | |
|
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት የሱዳን የጦር ኃይል አባላት በቅርቡ በአገሪቱ በስተምዕራብ ባካሄዱት ጦርነት የአስገድዶ መድፈር ጥቃት አድርሰዋል ማለቱን በመጥቀስ የሱዳን መንግሥት ሪፖርቱ ከእውነት የራቀ በማለት ማጣጣሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በተመድ ሪፖርት መሰረት የሱዳን መንግሥት በአካባቢው ባካሄደው ጦርነት ከአንድ መቶ አስራ አምስት በላይ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ሪፖርቱ የአይን እማኞችን በመጥቀስ የሱዳን የጦር ኃይል አባላት ሴቶቹን አስገድደው መድፈራቸውን አትቷል፡፡ የሱዳን መንግሥት በበኩሉ የተመድ ሪፖርት ሆን ተብሎ የሱዳንን መንግሥት ለማጥቃት የተሰነዘረ ፕሮፖጋንዳ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የሱዳን ወታደሮች በአካባቢው የሚገኙትን ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት እንዳይደርስባቸው ማድረጉንና የአማጺ ኃይሎችን በመለየት ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል፡፡ በሱዳን ዳርፉር እ.ኤ.አ ከ2003 ጀምሮ በተካሄደው ጦርነት ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውንና ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተመድ ሪፖርት አስታውቋል፡፡ የዙምባብዌ ተቃዋሚዎች መንግሥት ምርጫውን ለማጭበርበር መዘጋጀቱን አስታወቁ የዙምባብዌ ተቃዋሚዎች መንግሥት ምርጫውን ለማጭበርበር ተዘጋጅቷል በማለት መንግሥትን መወንጀላቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ አመለከተ፡፡ በዘገባው መሠረት ተቃዋሚዎች ምርጫው ከወዲሁ እየተጭበረበረ መሆኑን መግለፃቸው ታውቋል፡፡ ተቃዋዎች የአገሪቱ መንግሥት ለአምስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን መራጮች ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ የምርጫ ካርድ ማዘጋጀቱን በመጥቀስ መንግሥት ምርጫውን ለማጭበርበር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በበኩሉ ተጨማሪ የምርጫ ካርድ በምርጫ ወቅት አስፈላጊ መሆኑንና ምርጫው እንደማይጭበረበር አስታውቋል፡፡ ..ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ.. ሲሉ የምርጫ ኮሚሽን ተጠሪ ጆርጅ ቺዊሶ አስታውቀዋል፡፡ ሂዝቦላ በቤሩት የድጋፍ ሰልፍ ጠራ ሂዝቦላ ደጋፊዎቹ በቤሩት የድጋፍ ስብሰባ እንዲያካሂዱ ጥሪ አስተላለፈ፡፡ በስብሰባው የኢማን መጉናይ የአርባ ቀን የሐዘን መታሰቢ ስነስርዓት ይጠናቀቃል፡፡ የሂዝቦላ መሪ የነበሩት ኢማን መጉናይ በደረሰባቸው የቦንብ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን አስመልክቶ ሂዝቦላ ያወጀው የአርባ ቀን የሐዘን መታሰቢያ ስነስርዓት ያለፈው ሰኞ ተጠናቋል፡፡ ይህንን ተከትሎ ሂዝቦላ ደጋፊዎቹ የድጋፍ ሰልፍ እንዲያካሂዱ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ በኢማን መጉናይ ላይ ለደረሰው ሞት እስራኤል ተጠያቂ መሆኗን ሂዝቦላ ማሳወቁን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡ በፓኪስታን የጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ ሊካሄድ ነው የፓኪስታን ፓርላማ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለመምረጥ ስብሰባ ሊያካሂድ መሆኑን የአሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ አመለከተ፡፡ በቅርቡ በአገሪቱ የተደረገውን የፓርላማ አባላት ምርጫ በበላይነት ያሸነፈው የፓኪስታን ህዝቦች ፓርቲ ተወካይ የሱፍ ራዛ ጂላኒ እንደሚመረጡ ይጠበቃል፡፡ በምርጫው በአገሪቱ ከአስራ ሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመንግሥትን የመሪነት ሰልጣን ከፕሬዚዳንት ሙሻራፍ ፓርቲ እጅ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |