| ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር በቀርከሃ ልማት... |
|
|
| Wednesday, 26 March 2008 | |
|
ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር በቀርከሃ ልማት ተባብራ ለመስራት ፍላጎት አላት
ኢትዮጵያ ከህንድ ጋር በቀርከሃ ልማት ተባብራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡ ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የቀርከሃ ልማት ማካሄድ የሚያስችል እምቅ ሀብት ያላት ሀገር መሆኗ ይህን ሀብት በአነስተኛም ሆነ በመካከለኛ ኢንዱስትሪ ለማልማት ፍላጎት መኖሩን፣ ለዚህ ደግሞ ህንድ ያላትን ልምድ በማካፈል ኢትዮጵያን በዘርፉ ልትረዳ እንደምትል ተገል..ል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው የቀርከሃ ልማት ወደ 1 ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት የሚሸፍን ሲሆን ከዚህ ውስጥ 8 በመቶው በቆላማ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚበቅል መሆኑን በቆላማ መሬቶች የሚበቅሉ የቀርከሃ ዝርያዎች ለዕደ ጥበባት ውጤቶች መስሪያ የሚውል ሲሆን በደጋማ አካባቢዎች የሚበቅሉት ደግሞ ለወረቀት ኢንዱስትሪ የሚሆኑ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ቀርከሃ በብዛት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ እየጨመረ በመጣው በኢንዱስትሪና የቤት ግንባታ ሳቢያ በከፍተኛ ሁኔታ በጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡ ለቲቪ ህሙማን የ60 ሚሊዮን ብር መድሀኒት አገር ውስጥ ገብቷል በተያዘው ዓመት ለሳንባ ነቀርሳ /ቲቢ/ ህሙማን የሚያገለግል 60 ሚሊዮን ብር የሚገመት መድሀኒት ከውጭ ተገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ መድሀኒቱ 68 ሺህ ለሚሆኑ የቲቢ ህሙማን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡ መድሀኒቱ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በሚገኙ የጤና ድርጅቶች እንዲሰራጭ መደረጉን፣ ሚኒስቴሩ ቲቢን በመከላከሉና መቆጣጠሩ ረገድ ጥራቱን የጠበቀ የዶትስ ህክምና የማስፋፋትና የማጠናከር፣ የጤና ስርዓቱን የማጎልበት እንዲሁም በመስኩ ጥናትና ምርምሮችን የማበረታታት ሥራ በማከናወን ላይ መሆኑን፣ በዚህ ዓመትም አገልግሎቱን በማሳደግ 60 በመቶ የሚሆኑ የሳንባ ህሙማን በሚሊኒየሙ ጸረ ቲቢ ዘመቻ ለማከም ከፍተኛ ግብ የተጣለ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የቲቢ መድሀኒት መውሰድ የጀመረ ሰው በሀኪም የታዘዘለትን መድሀኒት ማቋረጥ እንደሌለበትና መድሀኒቱ ከተቋረጠ ተህዋስያኑ መድሀኒቱም መላመድ ስለሚጀምሩ ህመምተኛው ባሉት መድሀኒቶች ሊድን እንደማይችል መድሀኒቱን ያቋረጠ ህመምተኛ ወዲያውኑ ለጤና ተቋማት ሪፖርት ማድረግ እንደሚኖርበት፣ ማንኛውም መድሀኒቱን መውሰድ የጀመረ የቲቢ ህመምተኛ ለስምንት ወራት የታዘዘለትን መድሀኒት በአቅራቢያው ከሚገኙ የጤና ድርጅቶች በነፃ ማግኘት ይችላል ብሏል፡፡ የዘንድሮው የዓለም ቲቢ ቀን በኢትዮጵያ ለ11ኛ ጊዜ የፊታችን መጋቢት 15 ቀን 2000 ዓ.ም ተከብሮ ይውላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአፋር ብሄራዊ ክልል የሥራ ጉብኝት አደረጉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ጉብኝቱ በተንዳሆ ግድብና መስኖ ፕሮጀክት ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተንዳሆ ቤቶች ልማት ፕሮጀክትና የአፋምቦ ወረዳ የግብርና ልማት እንቅስቃሴንም ጎብኝተዋል፡፡ ከአገሪቱ ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነውና ከአዲስ አበባ በ580 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው የአዋሽ ወንዝ ላይ የሚካሄደው የተንዳሆን ግድብና መስኖ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ መንግሥት ከአንድ ቢሊዮን 800 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ወጪ የተደረገበት ነው፡፡ የተንዳሆ ግድብና የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ በ1999 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ በ60 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ ለማልማት የሚያስችል ሸንኮራ አገዳውም በክልሉ ለሚቋቋመው የስኳር ፋብሪካ ግብዓት እንደሚሆን ታውቋል፡፡ ፋብሪካው ሲቋቋም በዓመት ከ722 ሺህ ቶን በላይ ስኳር የማምረት አቅም ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የጎበኙት ሌላው ፕሮጀክት ደግሞ በመንግሥት በአንድ ቢሊዮን 700ሺህ ብር ወጪ የሚካሄደው የተንዳሆ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ነው፡፡ በፕሮጀክቱ 17 ሺህ ያህል የመኖሪያ ቤቶች የሚገነቡ ሲሆን እስካሁን የአንድ ሺህ ያህል ቤቶች ሥራ ተጠናቋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |