| አውሮፕላን ውስጥ ሞባይል ስልክ መጠቀም ተፈቀደ |
|
|
| Wednesday, 26 March 2008 | |
|
የዱባይ አየር መንገድ ቅርንጫፍ የሆነው የኢምሬትስ አየር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳፋሪዎች አውሮፕላን ውስጥ የሞባይል ስልካቸውን እንዲጠቀሙ ፈቅዷል፡፡
አየር መንገዱ የሞባይል ጥሪ አውሮፕላን ውስጥ እንዲቀበሉ ለተሳፋሪዎች ፈቃድ የሰጠው ከዱባይ እስከ ካዛብላንካ ባለው መስመር ነው፡፡ በተለያዩ አውሮፕላኖች ውስጥ ሲስተሙን ለመዘርጋት እቅድ መያዙንም አየር መንገዱ አመልክቷል፡፡ ተሳፋሪዎች የሞባይል ጥሪ መቀበል የሚችሉበት ጊዜም ተወስኖላቸዋል፡፡ አውሮፕላኑ መደበኛ በሆነ ፍጥነት እየበረረ ባለበት ወቅት ሞባይል ማናገር የሚፈቀድላቸው ሲሆን የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ሲስተሙ ጥቅም ላይ ሲውል መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጥሪ ከመቀበል በተጨማሪ ተሳፋሪዎቹ የፅሁፍ መልዕክቶችን መላክ እንደሚችሉ ተገል..ል፡፡ በማታ በረራ የሚደረጉ የስልክ ጥሪዎችን ግን የአውሮፕላኑ ሠራተኞች መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡ የስልክ ጥሪዎችን ለመቀበል ሞባይሎቻቸው ድመፅ የሚያሰሙበት ሙድ ላይ (silent mood) ላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህ በፊት አውሮፕላን ውስጥ የሞባይል ጥሪ መቀበል የሚከለከለው ከአውሮፕላኑ የድምፅ መልዕክት ማስተላለፊያ ሲስተም ጋር እንዳይጋጭ ነበር፡፡ ኤሮ ሞባይል በተባለው ኩባንያ ተሰርቶ የተዘጋጀውና በኢምሬትስ አየር መንገድ ጥቅም ላይ የዋለው ሲስተም ሞባይሉም ሆነ የአውሮፕላኑ ሲስተም ሳይጋጩ ሥራ ላይ እንዲውሉ የሚያስችል ነው፡፡ ሲስተሙ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ግን አየር መንገዱ ከዓለም አቀፍ የአየር መንገድ ደህንነት ድርጅት ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ የኢምሬት አየር መንገድ በዱባይ መንግሥት ስር የሚተዳደር ሲሆን 60 ወደሚደርሱ ሀገራት ይበርራል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |