| "ሃይፐር አክቲቪቲ" የወጣት ሴቶች ችግር |
|
|
| Wednesday, 26 March 2008 | |
እረፍት የለሽ መሆን (ሃይፐር አክቲቪቲ) በተለይ በወጣት ሴቶች ላይ የሚከሰት ችግር መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ፡፡ ከ10 ያህል ሴቶች አንዷ የችግሩ ተጠቂ ናት፡፡ ችግሩ በተለይ በወጣትነት ዘመናቸው ጎልቶ እንደሚታይ ነው ጥናቱ የሚጠቁመው፡፡ጥናት ከተካሄደባቸው ከ25 ዓመት በታች በሆኑ 800 ያህል ሴቶች ሃይፐር አክቲቭ (እረፍት የለሽ ቀዥቃዣ) የሆኑት ከሥራ አጥነት፣ ከጥቃት ጋር፣ በታዳጊነት ከሚከሰት እርግዝና ጋር የተያያዘ እንደሆነ ታውቋል፡፡ በቅርቡ ሃይፐር አክቲቭ የሆኑ ልጆች ላይ የተደረገው ጥናት ደግሞ በሽታው መታከምና የልጆቹን ባህሪ ማስተካከል እንደሚቻል ጠቁሟል፡፡ በመሆኑም ወጣት ሴቶች በተለይ በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ከጅምሩ ታክመው መዳን እንዳለባቸው ጥናት አድራጊዎቹ አረጋግጠዋል፡፡ እድሜያቸው ከስድስት እስከ 12 በሚደርሱ ሴት ልጆች ላይ በየዓመቱ የሚደረገው ይህ ጥናት አብዛኞቹ ልጆች የሃይፐር አክቲቪቲ ምልክት የሆኑትን ያለእረፍት ወደ ላይና ወደ ታች መዝለል፣ አንዱን ሳይጨርሱ ሌላ ሥራን ለመሥራት መጣደፍ (ያዝ ለቀቅ ማድረግ"፣ ተረጋግቶ ቁጭ አለማለትና ያለማቋረጥ መለፍለፍ ታየቶባቸዋል፡፡ ልጆቹ እረፍት ከማጣታቸው በተጨማሪ ጠብ አጫሪና ተደባደቢም እንደሚሆኑ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ የሃይፐር አክቲቪቲ ችግር ተጠቂ የሆኑ ልጆች ከሌሎቹ ይልቅ በሁለት እጥፍ አጫሽነትን ጨምሮ ለተለያዩ ሱሶች የመጋለጥ፣ ጤናማ ያልሆነ ጓደኝነትን ለመመስረትና በትምህርት ቤትም ከሌሎቹ ይልቅ በአራት እጥፍ ዝቅተኛ ውጤት የማምጣት እድል እንደሚኖራቸው ጥናቱ አሳይቷል፡፡ እንግሊዝ ውስጥ በሴንት ጆርጅ የአዕምሮ ሕክምና ተቋም የሕፃናት ወጣቶች የስነልቦና አማካሪ ዶ/ር ሞሪስ ዝዊ እንደሚሉት ሃይፐር አክቲቭ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚታየው የህይወት ቀውስ በወንዶች ላይም ይከሰታል፡፡ ደብሊው ኤች ኦ አጫሽ የሕንድ ታዳጊዎችን አስጠነቀቀ ሕንድ ውስጥ ከአምስት ታዳጊ ሴቶች መካከል አንዷ የትምባሆ ተጠቃሚ መሆኗን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡ በመሆኑም ከአጫሽነት ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች በስፋት ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ በመግለፅ ወጣቶቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አስጠንቅቋል፡፡ ድርጅቱ በ14ዐ ያህል ሀገራት የዳሰሳ ጥናት ያካሄደ ሲሆን የሕንድ ሪፖርቱ እንደሚያሳየው 17 በመቶ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎች የቶባኮ ተጠቃሚዎች ናቸው፤ አብዛኞቹም የሚያጨሱት ሲጋራ ነው፡፡ ጥናቱ እንደሚያሳየው ከመካከለኛው ሕንድ በስተቀር በሌሎች በሀገሪቱ አካባቢዎች ትምባሆ ተጠቃሚ በሆኑ ሴቶችና ወንዶች መካከል እምብዛም የቁጥር ልዩነት አይስተዋልም፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች የቶባኮ ተጠቃሚ ሴቶች ቁጥር መጨመር አሳሳቢ መሆኑን ሪፖርቱ ሳይጠቁም አላለፈም፡፡ ተማሪዎች የትምባሆ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ በሥነምግባር የመኮትኮት ኃላፊነት የተጣለባቸው አስተማሪዎቻቸውም አጫሾች በመሆናቸው ተማሪዎቹን እያበረታታ መሆኑን ነው ጥናቱ ያሳየው፡፡ የሳተርን ጨረቃ ድብቅ ውቅያኖስ ሳይኖረው አይቀርም ቲታን በመባል የሚታወቀው የሳተርን ጨረቃ ጥልቅና ድብቅ ውቅያኖስ ሳይኖረው እንደማይቀር ተገምቷል፡፡ ካዚኒ ሃይጅንስ ማሽን በሚል ተልዕኮ በሚካሄደው የራዳር ምስል ዳሰሳ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፣ ከጨረቃዋ የፊት ለፊት ገፅታ በረዶ ሰር ሰፊ የውሃ ይዞታ ያለው ቦታ እንዳለ ያሳያል፡፡ ይህ እርግጠኛ ከሆነም ቲታን ለሕይወት ወሳኝ የሆኑ ሁለት ነገሮችን ውሃና ኦርጋኒክ ሞሎኪውሉን ይዟል፡፡ ካዚኒ ሃይጅንስ ማሽን በአሜሪካው የህዋ ኤጀንሲ (ናሳ"፣ ከአውሮፓ የህዋ ኤጀንሲ (ኢሳ) እና ከጣሊያ የህዋ ኤጀንሲ (አሲ) ትብብር የሚሰራ ፕሮጀክት ነው፡፡ በቅርቡም ከሶላር ሲስተም ጥልቅ ውቅያኖስ አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ (ጋኒሜድ፣ ካሊስቶና ኢሮፓ የሚባሉ) ሦስት ቦታዎች በራዳር ምስሉ መጠቆሙ ታውቋል፡፡ የቲታን ውቅያኖስ አራተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ቱታን በሶላር ሲስተም ውስጥ ሁለተኛዋ ትልቁ ጨረቃ ስትሆን 50 በመቶ የሚሆነው ገፅታዋ በቀለጠ በረዶ ተሸፍኗል፡፡ ሙቀት በመጨመሩ የአሳዎች ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል አሳዎች በተለያዩ ምክንያቶች በዓለም ላይ ያላቸው ቁጥር እየቀነሰ ቢሆንም በዓለም አቀፉ ሙቀት መጨመር ምክንያት ህልውናቸው አደጋ ላይ እየወደቀ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ የባህሮች ሙቀት መጨመር የባህር ውስጥ አሳዎችን ህይወት አደጋ ውስጥ ጥሏል፡፡ እንደ ዘገባው ከሆነ ሌላው ለአሳዎች ህልውና አደጋ የሆነው የዓለም ሕዝበ ቁጥር መብዛት ነው፡፡ የቢቢሲ ዘገባ እንደሚያመለክተው ለአሳዎችና ለሌሎችም የባህር ውስጥ እንስሳት አደጋው እየበዛ ነው፡፡ ፀረ ተባይን ጨምሮ የተለያዩ ኬሚካሎች ወደ ውሃ ውስጥ ይለቀቃሉ፡፡ ኬሚካሎቹ ውሃውን በመበከል ለእንስሳቱ ህገወጥ አደጋ ከመሆናቸው በተጨማሪ ሊመገቧቸው የሚችሉ የባህር ውስጥ አትክልትንም ያጠፋሉ፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |