| በቴዲ አፍሮ ክስ የምስክሮችን... |
|
|
| Sunday, 30 March 2008 | |
በቴዲ አፍሮ ክስ የምስክሮችን ቃል ፍ/ቤት አዳመጠቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) “ሰለሜ” በሚለው የሙዚቃ አልበሙ የፈጠራ ሥራዬ የሆኑ ሥዕሎቼን ከፍቃዴና ከዕውቅናዬ ውጪ ተጠቅሟል በሚል ከቀረበበት የወንጀል ክስ ጋር በተያያዘ ፍ/ቤት የዐቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮች ቃል አዳመጠ፡፡ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው ዓርብ ዕለት ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን ሁለት ግለሰቦች ምስክርነት አዳምጠ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ፍ/ቤቱ በቀጣይ ቀጠሮው የዐቃቤ ሕግን በክሱ ላይ ያቀረበውን ማስረጃ መርምሮ ቴዲ አፍሮን ይከላከል ወይም መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ ይሰናበት የሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቴዲ አፍሮ በሰለሜ አልበሙ ሲዲ ውስጥ የፈጠራ ሥራዬን ከዕውቅናዬ ውጪ ተጠቅሟል በሚል የፈጠራው ሥራ ባለቤት ነኝ በሚሉ አቶ አዲስ ገብሩ ተከስሶ በዚህ ጉዳይ ፍ/ቤት ሲቀርብ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |