| ጋዜጠኞች ራሳቸውን የሚቆጣጠሩበት... |
|
| Wednesday, 09 January 2008 | |
|
ጋዜጠኞች ራሳቸውን የሚቆጣጠሩበት መንገድ ሊፈጥሩ ይገባል አዲሱ የፕሬስና የመረጃ ነፃነት ሕግ ያሉትን ለአሰራር የማያመቹ ሁኔታዎች ለማስወገድ ጋዜጠኞች ራሳቸውን በራሳቸው የሚቆጣጠሩበት መንገድ ሊያመቻቹ እንደሚገባ }ÑKì:: ¾ý_e IÓ ጋዜጠኞች እየሰሩ ያሉበትን ሁኔታ የሚለውጥ ሳይሆን የተሻለ መረጃ የማግኘት መብት ሚያጎናጽፍ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ በመረጃ ነፃነት ህግ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ኤክስፐርትና የደቡብ አፍሪካው ኦፕን ዴሞክራሲ አድቫይስ ሴንተር.. ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚ/ር ሙክላኒ ዲምባ ለሪፖርተር እንዳሉት በረቂቅ የመረጃና የፕሬስ ነፃነት ህጉ እንደተደረገው የፕሬስና የመረጃ ነፃነት ሕጉ ሁለቱን ጉዳዮች አንድ ላይ ማምጣቱ አግባብ ካለመሆኑም በላይ መረጃ ሲከላከል የሚጠየቀውን ይግባኝ ዳኞች እንዳያዩ መቀመጡ ተቀባይነት የለውም፡፡ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃንና የህግ ባለሙያዎች ክልከላን እንደሚያባብስ የተነገረለት ህግ ተግባራዊ እንዳይሆን ወይም እንዲሻሻል ጋዜጠኞች ምን ማድረግ ይችላሉ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም ..የፕሬስ ህግ አያስፈልግም ለማለት ራሱን በራሱ የሚያስተዳድር የተጠናከረ አካል (ፕሬስ ካውንስል) ያለው ጋዜጠኛ ያስፈልጋል.. ካሉ በኋላ በአገራቸው ደቡብ አፍሪካ ጋዜጠኛው ራሱን በራሱ የሚቆጣጠርበት ሁኔታ የተመቻቸ በመሆኑ የፕሬስ ህግ እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡ ሚ/ር ዲምባ አክለውም ረቂቅ ህጉ የመረጃ መብትና የፕሬስ ነፃነት የሚሉትን ሁለት የተለያዩ ጽንሰ ሃሳቦች አንድ ላይ ማምጣቱ ተገቢና የሚመከር አሰራር አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከመረጃ የማግኘት መብት አንፃር፣ ያሉበት ችግሮች እንዳሉ ሆነው፣ ሕጉ ዝቅተኛ የሚባለውን መስፈርት የሚያሟላ ቢሆንም ከፕሬስ ነፃነት አንፃር ግን ምንም ዓይነት ዝርዝር አንቀፆች አለማካተቱንም ያስረዳሉ፡፡ ሚ/ር ዲምባ አክለው እንዳሉት በረቂቅ ሕጉ አንቀጽ 23 መረጃ ሊከለከል የሚችልበት ሰፊ ዕድል የሚፈጥር ድንጋጌ መኖሩን ሲጠቅሱ እንደ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ያሉ እንዲሁም የሚኒስትሮች ምክር ቤትን የመሳሰሉ አካላት መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠቡ የሚፈጥር ዕድል መኖሩ የዚህ አንቀጽ ዝርዝሮች መብዛት የመረጃ ክልከላን ሊያባብስ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ እንደ ሚ/ር ዲምባ ገለፃ በረቂቅ ህጉ መረጃ የማግኘት መብትን ጋዜጠኞች ብቻ የሚጠቀሙበት አድርጎ የማየት አዝማሚያ ሲኖር ይልቁንም መረጃ ለመስጠት እስከ 30 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይበት ሁኔታ በመሆኑ ለምርመራ ጋዜጠኝነት ካልሆነ ለጋዜጠኞች መረጃ በወቅቱ ለማግኘት የሚያመች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአንፃሩ መረጃ የማግኘት መብት ማንኛውም ዜጋ ሊጠቀምበት የሚችል፣ ሙስናን ለማጣራትና ብልሹ አሰራርን ለማጋለጥ እንዲሁም ለሌሎችም ምክንያቶች ሊውል የሚገባ እንደሆነ ሚ/ር ዲምባ አስረድተዋል፡፡ ..ረቂቅ ሕጉ በተሻለ ሁኔታ ሊዘጋጅ ይችል ነበር.. ያሉት ኤክስፐርቱ በተለይ በፕሬስ ነፃነት በኩል ረቂቅ ሕጉ የፕሬስ ነፃነትን ለማረጋገጥ የማይችል ህግ ነው ብለዋል፡፡ ..እንዳለመታደል ሆኖ በአፍሪካ ሚዲያ በዲሞክራሲ ግንባታና በሌሎች የዕድገት ሂደቶች ሊጫወት የሚችለውን ወሳኝ ሚና ለመወጣት አልቻለም.. ያሉት ሚ/ር ዲምባ አሁንም በርካታ የአፍሪካ አገሮች መንግስትን የማይደግፉ ዘገባዎች በማውጣታቸውና ሥራቸውን በመስራታቸው ብቻ ጋዜጠኞች ለእስርና ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ሚ/ር ዲምባ እንዳሉት በአፍሪካ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኡጋንዳ የመረጃ ነፃነትን ህግ አውጥተው ተግባራዊ በማድረግ ላይ ያሉ ሲሆን በአግባቡ በመተግበር ግን ደቡብ አፍሪካ ብቸኛ አገር ናት፡፡ በቤተልሔም ነጋሽ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |