Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow ቴሌና ተጠቃሚዎች በሲም ካርድ...
ቴሌና ተጠቃሚዎች በሲም ካርድ... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
ቴሌና ተጠቃሚዎች በሲም ካርድ አቅርቦት ጉዳይ አልተስማሙም

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በበቂ ሁኔታ የሞባይል ሲም ካርድ ማቅረብ ባለመቻሉ መቸገራቸውን ተጠቃሚዎች ገለፁ፡፡ ቴሌ የሲም ካርድ አቅርቦት ችግር እንደሌለ አስታውቋል፡፡
አገልግሎት የተጓደለባቸው ተጠቃሚዎች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንዳስታወቁት ኮርፖሬሽኑ የሲም ካርድ ችግር እንደሌለ በተደጋጋሚ ቢገልፅም ገበያ ላይ ማግኘት አልቻሉም፡፡

የሞባይል ስልክ አስፈላጊ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ የተጠቃሚዎችን ፍላጐት ማርካት አለመቻሉ ቅር እንዳሰኛቸው የገለፁት አገልግሎት ጠያቂዎች “ኮርፖሬሽኑ አስቸኳይ መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል” ብለዋል፡፡

የተገልጋዮች አቤቱታን አስመልክቶ ኮርፖሬሽኑ እንዳስታወቀው ችግሩ የሞባይል ሲም ካርድ ሳይሆን በክልል ከተሞች ያለው የኔትወርክ አቅም አለመሟላት ነው፡፡

ቀደም ሲል ለክልሎች የተገነባው አቅም የማስፋፊያ ሥራ ስላልተሰራለት ከአዲስ አበባ ሲም ካርድ የሚገዙ ተገልጋዮች ወደ ክልል እየወሰዱ መጨናነቅ በመፍጠራቸው ሳቢያ በአዲስ አበባ ሲም ካርድ ሽያጭ እንዲቆም መደረጉን፣ ሽያጩ እንዲቆም የተደረገውም ለጊዜው እንደሆነ ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡

በቬንደር ፋይናንሲንግ ከተገኘው ገንዘብ ውስጥ 5.6 ሚሊዮን የሞባይል ደንበኞችን ማስተናገድ የሚያስችል ስምምነት ከዜድ ቲ ኢ ኩባንያ ጋር በየደረጃው መደረጉን ኮርፖሬሽኑ ገል..ል፡፡

በዚሁ መሠረት 1.2 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማስተናገድ ታስቦ በሚሌኒየም ፕሮጀክቱ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ እቅዱ ተግባራዊ መሆኑን ያመለከተው ኮርፖሬሽኑ 4.4 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማስተናገድ በተመረጡ 15 የክልልና የንግድ ማዕከል በሆኑ ከተሞች የኔትወርክ ማስፋፊያ ሥራ መጀመሩን ገል..ል፡፡

የሦስተኛው ትውልድ (ዘመናዊ አገልግሎቶች) መስጠት የሚያስችል 250 ሺ የሞባይል ሲም ካርድ ተዘጋጅቶ የሙከራ ሥራው ተጠናቆ በርክክብ ላይ መሆኑን፣ 250 ሺ የገመድ አልባ ስልክ ሲም ካርድም በተመሳሳይ መልኩ ለተጠቃሚው ለማድረስ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >