| ስኳር ከውጪ ተገዝቶ መግባት ይጀምራል |
|
|
| Sunday, 30 March 2008 | |
![]() አቶ ግርማ ብሩ የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከትላንትና ጀምሮ የፓልም ዘይትን ሙሉ በሙሉ ከታክስ ነጻ ሲያደርግ የልብስ ሳሙና ላይ ተጥሎ የነበረው ሱር ታክስ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ የስኳር ፍላጎት ላይ እጥረት እንዳይከሰት 1.5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ወደ አገር ውስጥ ይገባል፡፡ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አቶ ግርማ ብሩ አርብ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፓልም ዘይት ሙሉ በሙሉ ከታክስ ነፃ መደረጉን፣ በደረቅና በዱቄት የልብስ ሳሙና ላይ ተጥሎ የነበረው የሱር ታክስ ከትላንት ጀምሮ መነሳቱን አስታውቀዋል፡፡ አቶ ግርማ ብሩ በመጪው የክረምት ወራት ምክንያት የስኳር ምርት እጥረት እንዳይከሰት ሲባል ከውጭ አገር 1.5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ግዢ እንደሚፈጸም ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ አራት መቶ ሺ ኩንታል ስኳር ግዢ የጨረታ ስርዓቱ ተጠናቆ በመጪው ሚያዚያ ወር ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ ቀሪው 1.1 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በሚቀጥለው አርብ በሚከፈተው የጨረታ ስነስርዓት ግዢው ይፈፀማል፡፡ መንግሥት የዘይት ዋጋ ንረትን ለመቀነስ 10 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ገዝቶ በጅንአድና በሌሎች የጅምላ አከፋፋይ ነጋዴዎች አማካኝነት ያሰራጫል፡፡ መንግሥት የፓልም ዘይትን ሙሉ በሙሉ ከታክስ ነፃ በማድረጉ ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን ብር የታክስ ገቢ እንደሚያጣ አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር በእህል ገበያው ከማረጋጋት አንፃር ገብስና ማሽላ ወደ ውጭ እንዳይላኩ መከልከሉን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ በተሾመ ንቁ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |