Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow በመዲናዋ የሚገኙ ሶስት ሆስፒታሎች...
በመዲናዋ የሚገኙ ሶስት ሆስፒታሎች... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
በመዲናዋ የሚገኙ ሶስት ሆስፒታሎች የሙስና ችግር እንዳለባቸው ተረጋገጠ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙት የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል፣ የካቲት 12 ሆስፒታል የሙስና ችግር እንዳለባቸው የሙስና እና ብልሹ አሠራር ስጋቶችን ለመከላከል የተካሄደ የአሰራር ሥርዓት ማሻሻያ ጥናት ሪፖርት አመለከተ፡፡
የካቲት 2ዐዐዐ ዓ.ም የቀረበው ይኸው ሪፖርት እንደሚያመለክተው በሶስቱም ሆስፒታሎች የህሙማን አልጋ አጠቃቀም የሥራ ሂደት ፍትሀዊነት የጐደለው ነው፡፡ ለታካሚዎች የሚሰጥ የአልጋ ቀጠሮ ወረፋ መጠበቂያ ቅደም ተከተል በጠበቀ ቁጥር አይከናወንም፡፡ የታካሚዎች ድልደላ በሀኪም መልካም ፈቃድ ብቻ እንዲያገኝ መደረጉም ድልድሉ ለአድልኦ የተጋለጠ እንዲሆን በር ከፍቷል፡፡

በሆስፒታሉ የአልጋ አሰጣጥ መመሪያ ላይ ለነፃ የሚፈቀደው ለሶስተኛ ማዕረግ አልጋ መሆኑን የጠቆመው ሪፖርቱ ለነፃ ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው በአንደኛ ደረጃ ማዕረግ አልጋ በመሆኑ አልጋ እስከሚገኝ ድረስ ታካሚዎች እንደሚጉላሉ የፌዴራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥረት ገል..ል፡፡

የሙስና ብልሹ አሰራር ችግር ተብሎ በሪፖርቱ ላይ የተገለጸው ሌላው ጉዳይ ተኝተው የሚታከሙ ህሙማን የምግብ፣ የመድሃኒትና የሌሎች አገልግሎቶች አቅርቦት ደካማ መሆን ነው፡፡

ለታካሚዎች የሚቀርብ ምግብ በሀኪሙ ትዕዛዝ /ሮቋ per the prescription of the ቅሻቨቋሽሰሽሮቃቋ/ ካለመሆኑም በላይ እያንዳንዱ ዋርድ አስቀድሞ የምግብ ፍላጐቱን ለምግብ ዝግጅት አያቀርብም፡፡ በሶስቱም ሆስፒታሎች ውስጥ በምግብ ዝግጅት ሙያ የሰለጠነ ባለሙያ አለመኖሩንና የምግብ እህል ዝግጅቱም የንጽህናና የጥራት ጉድለት ያለበት መሆኑን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡ የመድሀኒት ትዕዛዞችም በአግባቡ የማይከናወኑ በመሆኑ የቅዳሜና እሁድ መድሃኒት አርብ ወጪ የማድረግ አሠራር ለብክነት የሚዳርግ ሆኖ መገኘቱንም ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል፡፡

በሪፖርቱ ላይ እንደተጠቀሰው ህሙማን ገንዘብ ከፍለውና ካርድ አውጥተው ወደ ህክምና ክፍል ሲሄዱ ሀኪሙ ባለመኖሩ የሚጉላላበት ሁኔታ በስፋት ይታያል፡፡ በቀን አንድ የህክምና ባለሙያ ከ15-20 ህሙማን ማየት እንደሚገባው የተቀመጠ ስታንዳርድ ቢኖርም የየካቲት 12 ሆስፒታል ከአንገት በላይ ህክምና አገልግሎት ሁለት ሀኪሞች በቀን እስከ አምስት ታካሚ ብቻ በማየት ከሥራ ሰዓት በመቅረትና በፈረቃ በመሥራት ከሰዓት በኋላ በሥራ ቦታ አይገኙም፡፡ በዚህም ህሙማን በበሽታ ከመሰቃየታቸው በላይ ለእንግልትና በጉቦ ለመታከም አማላጅ ፍለጋ እንደሚሄዱ ተገደዋል፡፡

በራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ህሙማን ተኝተው የቀዶ ህክምና ሊደረግላቸው ሶስትና አራት ቀን ከቆዩ በኋላ የማደንዘዣ መርፌ ተወግተው ህክምና ሳያገኙ እንዲወጡ መደረጋቸውን የጥናት ቡድኑ ሪፖርት ያመለክታል፡፡

በአንድ ታካሚ ስም ተደጋጋሚ መድሃኒት በማዘዝ ለግል ጥቅም ማዋል፣ የህሙማንን ዝርዝር መግለጫ በቻርት ላይ በአግባቡ አለመሙላትና የላብራቶሪ አገልግሎት በተለያዩ ምክንያቶች በማሳበብ ወደ ግል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የመላክና ታካሚውን የማጉላላት አሠራር መከተል በጥናት ሪፖርቱ ላይ የቀረበው ሌላው የሶስቱ ሆስፒታሎች የሙስና ችግር ነው፡፡

የጥናት ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው በሆስፒታሎች ተኝተው የሚታከሙ ከፋይ ህሙማን በተለያዩ ማዕረጐች እንዲተኙ ሲታዘዝ ለማዕረጉ የታተመ ነውን ዋጋ በአግባቡ እንዲይዙ አይደረግም ለማዕረጉ የታተመ ነውን ገንዘብ አስይዘው ከተኙ በኋላም በህክምና ላይ ሲቆዩ ተጨማሪ ገንዘብ ማስያዝ ሲያስፈልግ ተከታትሎ የሚያስጨምር አካል የለም፡፡ ጉዳዩን በባለቤትነት አካል ባለመኖሩም ታካሚዎች ህክምናቸውን ተከታትለው ሲጨርሱ ያለባቸውን ቀሪ ገንዘብ ሳይከፍሉ የሚወጡ ታካሚዎችን እና የመሳሰሉትን ችግሮች ለመቆጣጠርና ለመከላከል የሚያስችል አሰራር አይታይም፡፡

የመንግሥትና የግል ጤና ኮሌጆች ተማሪዎች ለተግባር ስልጠና ወደ ሶሶቱም ሆስፒታሎች እንደሚሄዱ፣ የገለጸው ሪፖርቱ ለተግባር ስልጠና የሚሄዱት ተማሪዎች ሆስፒታሎች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የጥናት ሪፖርቱ እንደሚገልጸው ወጥነት ያለው የክትትልና ድጋፍ አንዲሁም የተግባር ስምሪት በተገቢው መንገድ ባለመኖሩ ተለማማጆች ከሆስፒታል ማግኘት ያለባቸውን ልምድ እንዳያገኙ ሆነዋል፡፡

አንዳንድ ተለማማጅ ተማሪዎች ለታካሚዎች ጉዳይ እናስፈጽማለን በማለት የተለያዩ ጥቅሞች ለማግኘት ሲሯሯጡ እንደሚታዩም የጥናት ቡድኑ ሪፖርት ይገልፃል፡፡

በኃይሌ ሙሉ
 
< Prev   Next >