Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow የሼህ አል-አሙዲ ምስል ከአዲስ አበባ...
የሼህ አል-አሙዲ ምስል ከአዲስ አበባ... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
Imageየሼህ አል-አሙዲ ምስል ከአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲነሳ ተጠየቀ
- ኮንፌዴሬሽኑ ካልተስማማ የባለሀብቱ ምስል በመጋረጃ ይሸፈናል

የሼህ መሀመድ ሁሴን አልአሙዲ ምስል ከአዲስ አበባ ስታዲየም ሳይነሳ የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች እንዳይካሄድ ጥያቄ እንደሚያቀርብ የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽንን እንደሚጠይቅ ተገለፀ፡፡
የሼክ መሀመድ ሁሴን አልአሙዲንን ምስል ጨምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያሉ ማስታወቂያዎች ሙሉ በሙሉ እንዲነሱ የሚደረገው የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሽን በጠየቀው መሠረት ነው፡፡

የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን ጉዳዩን አስመልክቶ በተደጋጋሚ ደብዳቤ መፃፉን አስታውሶ እ.ኤ.አ ፌብሩዋሪ 27/2008 ለውድድሩ አዘጋጆች በፃፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ማስታወቂያዎቹ እንዲነሱ የጠየቀው ኢትዮጵያ ውድድሩን ለማዘጋጀት ስትስማማ በገባችው ውለታ አንቀጽ 15 መሠረት ነው፡፡

አንቀጹ በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ወቅት ውድድሩ በሚካሄድበት ስታዲየም ውስጥ ኮንፌዴሬሽኑ የማያውቀው ማንኛውም ዓይነት ማስታወቂያ መለጠፍን ይከለክላል፡፡ ውድድሩን ስፖንሰር ለማድረግ ፈቃድ ያገኙ ድርጅቶችም ቢሆኑ በኮንፌዴሬሽኑ የማስታወቂያ ህግ መሠረት መስፈርት ወጥቶላቸው ሜዳው ዙሪያ እንጂ ስታዲየሙ አናት ላይ እንዲለጥፉ አይፈቀድም፡፡

ኮንፌዴሬሽኑ በጃንዋሪ 1/2008 “regulations governing advertising and promotional display under IAAF rule” በሚል አሻሽሎ ባወጣው የማስታወቂያ ህግ ቁጥር 8 መሠረት ከስፖርት መርህ ጋር የማይጣጣሙ ከሲጃራ፣ ከአልኮልና ከአበረታች መድሀኒቶች ማስታወቂያዎች በተጨማሪ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሀይማኖት ተቋሞችና ግለሰቦችን የሚያስተዋውቁ ማስታወቂያዎች በውድድሩ ወቅት እንዳይለጠፉ ይከለክላል፡፡

በኮንፌዴሬሽኑ የማርኬቲንግና የፕሮሞሽን ዳይሬክተር ፊርማ የተላከው ደብዳቤ ይህንኑ መሠረት በማድረግ በስታዲየሙ ውስጥ የተለጠፉ ማንኛውም ዓይነት ማስታወቂያዎች እንዲነሱ ያሳስባል፡፡

የሎካል ኦርጋናይዜሽን ኮሚቴ አባልና የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታሁን ገ/ጊዮርጊስ ጉዳዩን አስመልክቶ ለተጠየቁት “በቅርቡ ተልከው ከኮንፌዴሬሽኑ ከሚመጡ አካላት ጋር ውይይት ይደረጋል” ሲሉ ጥያቄው መቅረቡን ጠቅሰው መልስ ሰጥተዋል፡፡

በስታዲየሙ ውስጥ ያሉት ማስታወቂያዎች ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው አቶ ጌታሁን አስታውሰው “ከኮንፌዴሬሽኑ ተወካዮች ጋር በሚደረግ ወይይት ስምምነት ላይ ይደረሳል” ብለዋል፡፡

በስታዲየሙ ውስጥ “Long live Alamudi” በሚል የቀስተ ደመና ስፖንጅ ፋብሪካ የድርጅቱን ስም ጠቅሶ የለጠፈው የሼክ አልአሙዲ ምስልን በተመለከተ “እስካሁን ድረስ ለእንግዶች ማረፊያ ሸራተንን እየፈቀዱልን ስለሆነ የኮንፌዴሬሽኑን አባላት አሳምነን ምስላቸው ባለበት እንዲቀመጥ እናደርጋለን” ያሉት አቶ ጌታሁን “ኮንፌዴሬሽኑ ፈቃደኛ ካልሆነስ?” በሚል ለተጠየቁት “ውድድሩ ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ምስሉ በመጋረጃ እንዲሸፈን ይደረጋል” የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ አያይዘውም ከባለሀብቱ ጋር ውድድሩን ስፖንሰር በሚያደርጉበት አግባብ ላይ ውይይት በማድረግ ሌላ አመራጭም እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >