Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Wednesday
Aug 20th
Home arrow Sections arrow በአዲስ አበባ ለ52 ድርጅቶችና...
በአዲስ አበባ ለ52 ድርጅቶችና... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
በአዲስ አበባ ለ52 ድርጅቶችና ግለሰቦች መሬት ተፈቀደ

ከቀጣይ ወር የአካባቢና የማሟያ ምርጫ በኋላ የሚሰናበተው የአዲስ አበባ ከተማ ጊዜያዊ ባለአደራ አስተዳደር ከመስከረም እስከ የካቲት 2000 ዓ.ም. ድረስ መሬት እንዲሰጣቸው የተወሰነላቸውን 52 ያህል ድርጅቶችና ግለሰቦች ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡

የአስተዳደሩ መሬት ልማትና አስተዳደር ቦርድ መሬት እንዲሰጣቸው ባለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ ጊዜያት ወሰነላቸው ባለጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኀበር ከሊዝ ነፃ በአራዳ ክፍለ ከተማ 286 ካሬ ሜትር ቦታ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በቦሌ ክፍለ ከተማ በካሬ ሜትር 287.45 ብር ሂሳብ 5ዐ ሺ ካሬ ሜትር ቦታ፣ የአፍሪካ ኀብረት ለሆቴል ግንባታ የሚውል ከሊዝ ነፃ 118 ሺ 827 ካሬ ሜትር ቦታ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ለዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ የሚውል ከሊዝ ነፃ 110 ሺ 126 ካሬ ሜትር ቦታ በቦሌ ክፍለ ከተማ እንዲወስዱ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

የሊዝ ቦርዱ መሬት ከፈቀደላቸው ግለሰቦች መካከል ሼህ ኤልያስ ሬድዋን የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ጉባዔ ምክትል ሊቀመንበር በቦሌ ክፍለ ከተማ 500 ካሬ ሜትር ቦታ በካሬ ሜትር ብር 559.80 ሒሳብ እንደተፈቀደላቸው ይጠቁማል፡፡

የአስተዳደሩ ሊዝ ቦርድ መሬት ለማግኘት ካመለከቱ በርካታ ድርጅቶችና ግለሰቦች መካከል “ተፈቅዶላቸዋል” በሚል የዘረዘራቸው የተመረጡበት መስፈርት ምን እንደሆነ የጠቀሰው ነገር የለም፡፡

አስተዳደሩ የስም ዝርዝራቸው የተጠቀሱት ግለሰቦችና ድርጅቶች ቀርበው ውል እንዲፈፅሙ አሳስቧል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >