Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ከተሞች የመገበያያ...
ከተሞች የመገበያያ... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
ከተሞች የመገበያያ ማዕከላት ሥራ ሊጀምሩ ነው

መንግሥት የምርት ገበያን በስርዓት ለመምራት እንዲቻል በወሰደው እርምጃ መሰረት በስድስት ከተሞች የመገበያያ ማዕከላት በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎችም ዋጋን ለማረጋጋት የጎላ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
 
የመገበያያ ማዕከላቱን ሥራ ለማስጀመር እንዲቻል የተለያዩ የጥራትና ደረጃ መለኪያ መሳሪያዎች እየተሟሉላቸው እንደሚገኙ የገበያ ማዕከላቱ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት አማካኝነት እየተደራጁ መሆናቸውን፣ ማዕከላቱ የተቋቋሙትም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ነቀምት፣ ቡሮ ጎጃምና ዑመራ አካባቢዎች መሆኑን ተገልጿል፡፡

በሂደት ባህላዊውን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ስርዓት በዘመናዊ የግብይት ስርዓት ለመተካት በሚደረገው ጥረት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖው በታመነበት ተግባር ለሚሳተፉ ግለሰቦችና ነጋዴዎች ዕውቅና እየሰጠ መሆኑም ተገልጿል፡፡

-----------
በዓለም ባንክ 70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ ነው

በዓለም ባንክ የትምህርት ለሁሉም ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ትምህርት አገልግሎት የሚውል የ70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ወሰነ፡፡

እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡና የሚሌኒየሙን የትምህርት ግብ ለማሳካት በተሰራው ሥራ የተገኘው ውጤትና ለቀጣይ የተጠቀሱ የትምህርት ማስፋፋትና ጥራት የመጠበቅ አቅጣጫዎች የኢትዮጵያን የትምህርት ሁኔታ ለመለወጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያ በቀጣይ ሶስት ዓመታት ማለት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2010 ድረስ በትምህርት ዘርፍ ለማከናወን ያቀዳቸውን ተግባራት ማስፈጸሚያ የሚውል የ70 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ የድርጅቱ የድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሚስተር ጆይ ፋሚፊ አስታውቀዋል፡፡

-----------
የ2007 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በአዲስ አበባ ተገኝተው በዓለም የአየር ለውጥ ላይ ንግግር ያደርጋሉ

የ2007 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ዶክተር ራጀነድራ ኬ ፓቻኡሪ አዲስ አበባ ውስጥ በሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ፣ የፕላኒንግ እና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሮች የጋራ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ የዓለም የአየር ፀባይ ለውጥን በማስመልከት ንግግር እንደሚያደርጉ ታወቀ፡፡

በአፍሪካ አዳራሽ በሚካሄደው ስብሰባ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ዶክተር ራጀንድራ ኬ ፓቻኡሪ የዓለም አየር ለውጥን በተመለከተ ሰፊ ገለጻ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

ባለሙያዎች ወላጅ አልባ ሕፃናትን ለመርዳት የሚደረገውን ጥረት ሊያግዙ ይገባል፡፡ የኪነጥበብና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ወላጅ አልባ ሕፃናትን ለመርዳት የሚደረገውን ጥረት ሊያግዙ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡


ኢትዮጵያ 650 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አገኘች

ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በተለይ በቂ ንጽህና ለማያገኙት 35 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ የሚውል 650 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ የሚውል አገኘች፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ዓለም ባንክና የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ለዚህ ተግባር የሚውል 50 ሚሊዮን ዶላር መርዳታቸውን፣ ያ እንዳለ ሆኖ፣ የኢትዮጵያን ንጽህና ሙሉ በሙሉ ለማዳረስ የሚውል፣ ዩኒሴፍ በተወካዩ አማካኝንት እርዳታውን ሰጥቷል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.2 ቢሊዮን ህዝብ ለንጽህና መጠበቂያ የሚውል እርዳታ ቢያገኝም 2.6 ቢሊዮን ሰዎቸና 980 ሚሊዮን ህፃናት እንደሚቀሩ ዩኒሴፍ ገልጿል፡፡
 
< Prev   Next >