Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በናይጄሪያ በኤች.አይ.ቪ ከሚጠቁ...
በናይጄሪያ በኤች.አይ.ቪ ከሚጠቁ... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
በናይጄሪያ በኤች.አይ.ቪ ከሚጠቁ መካከል 61 በመቶ ሴቶች ሆነው ተገኙ

በናይጄሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው መኖሩ ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ሴቶች መሆናቸውን የናይጄሪያ ብሔራዊ የኤች.አይ.ቪ መቆጣጠሪያ ኤጀንሲን በመጠቀስ ቫንጋርድ ሌጎስ ዘግቧል፡፡

 

የብሔራዊ ኤች.አይ.ቪ መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ ከብሔራዊ የሴቶች ካውንስል ጋር በመሆን ባዘጋጃው ስብሰባ፡፡ ይህ ሁኔታ በአፋጣኝ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሻሻል ካልቻለ አገሪቷ ወሳኝ የሆነውን የሕብረተሰብ ክፍል የማጣት አደጋ እንደሚያጋጥማት አስጠንቅቋል፡፡

"ኤች.አይ.ቪን በመዋጋት ሴቶች ግንባር ቀደም መሆን እንደሚገባቸው እያንዳንዳችን ማበረታታት አለብን፡፡ ሰባ በመቶ ከሚሆኑ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ሰዎች የሚገኙት በአፍሪካ ነው፡፡ በናይጄሪያ ደግሞ በቅርብ በተደረገ የመረጃ ማሰባሰብ ስልሳ በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ልጃገረዶች ናቸው" ብለዋል፡፡

የኤጀንሲው ዳይሬክተር እንደገለፁት፣ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እንክብካቤና ድጋፍ በማድረግ ረገድ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ጫና አለ፡፡ ይህ ደግሞ በመላ አህጉሪቱ የተንፀባረቀ እውነታ ነው፡፡ ቫይረሱ ምን ያህል ሴቶችን እያጠቃ እንደሆነ ሲታይ የኤች.አይ.ቪን ስርጭት በመቆጣጠር እንቅስቃሴ ለምን ግንባር ቀደም መሆን እንዳለባቸው ያመለክታል፡፡

 
< Prev   Next >