Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ሴቶች ከእድሜ ጋር ግብግብ....
ሴቶች ከእድሜ ጋር ግብግብ.... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
ሴቶች ከእድሜ ጋር ግብግብ  እያደረጉ ነው

የውበት ባለሙያ ኤክስፐርቶች እንደሚሉት በእድሜ ምክንያት የሚከሰቱ የፊት ቆዳ ለውጦች አሜሪካውያን ሴቶችን የበለጠ ያስጨንቃቸዋል፡፡ በየቀኑ ስለፊታቸው ቆዳ መጨማደድ፣ ጥቁር ነጠብጣብ መውጣትና እድሜ ስላስከተለባቸው ለውጥ በጭንቀት ያወራሉ፡፡ እነኚህን ምልክቶች ለማጥፋትም በርካታ ሴቶች የፊት ቀዶ ሕክምና ያደርጋሉ፡፡ ይህንን በተመለከተ እንግሊዛውያን ሴቶች ተቃውሞ አላቸው፡፡

 

"ሴቶች የሚያደርጉት የፊት ቀዶ ሕክምና ከእድሜ ጋር የሚያደርጉት ግብግብ ነው" ይላሉ፡፡ 4 በመቶ የሚሆኑ እንግሊዛውያን ሴቶች እርጅናን ለመጋፈጥ የፊት ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ቢሆንም ብዙዎች ግን ይቃወሙታል፡፡

እርጅንና ለመዋጋት ተፈጥሯዊ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም እንደሚመርጡ የሚናገሩት እንግሊዛውያን ሴቶች፣ 56 በመቶ ያህሉ ማፅጃ፣ ቆዳ ማጠንከሪያ እንዲሁም ማለስለሻዎችን በመጠቀም በዕድሜ ምክንያት የሚመጡ የገፅታ ለውጦችን ለመከላከል የሚጥሩ ሲሆን 44 በመቶ ያህሉ ደግሞ ምግብና የሰውነት እንቅስቃሴ ይጨምሩበታል፡፡ 

 
< Prev   Next >