Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በአሥራ ዘጠኝ ከተሞች የአቅም....
በአሥራ ዘጠኝ ከተሞች የአቅም.... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
በአሥራ ዘጠኝ ከተሞች የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተካሄዱ ነው

በከተማ ልማት ዘርፍ በቀዳሚነት ድጋፍ በሚደረግላቸውና በአገር አቀፍ ደረጃ በሪፎርም ውስጥ በተካተቱ 19 ከተሞች ላይ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አስታወቁ፡፡

 

ኃላፊው አቶ መኮንን ብሩ እንዳመለከቱት የአቅም ግንባታ ሥራዎች ከሚካሄድባቸው መካከል 16ቱ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችና በትግራይ ክልሎች ይገኛሉ፡፡ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ ሐረር፣ አዲስ አበባና ድሬዳዋ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በእነዚህ ከተሞች ላይ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ሊካሄድባቸው የቻለው ከሀገሪቱ ከተሞች መካከል በቀዳሚዎቹ ደረጃ ላይ በመገኘታቸው፣ በሕዝብ ብዛታቸው፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ባላቸው ሚና፣ በስፋታቸው ወዘተ. በመመረጣቸው መሆኑን አቶ መኮንን አመልክተዋል፡፡

የክልል ከተሞች የመማርና የልምድ መቅሰሚያ ማዕከል መሆናቸው፣ ከዕድገታቸው፣ ከሚኖርባቸው ሕዝብ አንፃር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚታዩባቸው፣ የመሠረተ ልማት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቻቸውም በቅድሚያ ሊመለሱላቸው የሚገቡ ከተሞች መሆናቸው ለአቅም ግንባታ ሥራ ተመራጭ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡

የአቅም ግንባታ ፕሮግራም አገራዊ ይዘት እንዳለው፣ ለከተሞች አቅም ግንባታ ፕሮግራም ከተለያዩ በጎ አድራጊ መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በብድርና በዕርዳታ የሚገኘውን ፋይናንስ ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንደሚውል የመምሪያ ኃላፊው ጠቁመው የአቅም ግንባታ ሥራዎች በአብዛኛው የሚካሄዱት በዋናነት በፌዴራል መንግሥት በጀት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የአቅም ግንባታ ማለት በዋናነት በአሰራር፣ በአደረጃጀት እና በሰው ኃይል ልማት ላይ የሚያተኩርና በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚካሄደው የማስፈፀም አቅም ግንባታ ጋር የተያያዘ መሆኑን አቶ መኮንን ጠቁመው፣ "የከተሞች አቅም ግንባታ ልዩ የሚያደርገው ከከተሞች ልማትና መልካም አስተዳደር ጋር የተቀናጀ መሆኑና የላቀ ውጤት ያመጣሉ ተብለው በታዩ የከተማ ልማት ሥራዎች ላይ ያተኮረ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የከተማ ልማትን የሚመራ በቂ የሰው ኃይል ለማፍራት በታቀደው መሠረት በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የከተማ ሥራ አመራር ድህረ ምረቃ ፕሮግራም እንደተጀመረ፣ ኮሌጁም ባለፈውና በዚህ ዓመት በድምሩ አንድ ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ እንደሚገኝ፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ከጫጭር ሥልጠናዎች የተሞክሮ ልውውጥ መድረኮች እየተዘጋጁ ተፈፃሚ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡

 
< Prev   Next >