Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow ኢሠማኮ የንግድ ትርዒት ያካሂዳል
ኢሠማኮ የንግድ ትርዒት ያካሂዳል Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
የኢትዮጵያ ሠራተኞቸ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን 200 የሚደርሱ የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የንግድ ትርዒት ሊያካሄድ ነው፡፡

 

የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት የንግድ ትርዒቱ የሚካሄደው የዘንድሮውን የሜይዴይ በዓል ምክንያት በማድረግ ነው፡፡ የንግድ ትርዒቱ በሚሌኒየም አዳራሽ ከሚያዚያ 13 እስከ 23 ቀን 2000 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ከንግድ ትርዒቱ የሚገኘው ገቢ ኮንፌዴሬሽኑ በደብረዘይት ከተማ ግንባታው ለተጀመረው የአበራ ገሙ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ማሰልጠኛ ተቋም ወጪ ይውላል፡፡

ማዕከሉ ቀደም ብሎ ተይዞ በነበረ ግምት 31 ሚሊዮን ብር ይፈጃል ተብሎ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከዚህ በላይ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በሶስት ፌዝ የሚከናወን ሲሆን በመጀመሪያውና በሁለተኛው ፌዝ የሠራተኛ መሪዎች እና የሙያ ማሰልጠኛ ሕንፃዎች ግንባታ የሚያጠቃልል ሲሆን በሦስተኛው ፌዝ የኮሌጅ ግንባታ ይከናወናል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቦታው ላይ የመሰሰቢያ አዳራሽ ተገንብቶበታል፡፡  
በዳዊት ታዬ

 
< Prev   Next >