Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow የዋጋ ንረት መንስኤ ለማወቅ....
የዋጋ ንረት መንስኤ ለማወቅ.... Print E-mail
Sunday, 30 March 2008
የዋጋ ንረት መንስኤ ለማወቅ
ሁሉን አቀፍ ጥናት ያስፈልጋል


የዋጋ ንረቱ ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ሁሉን አቀፍ የሆነ ገበሬውን፣ ነጋዴውን፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጦችንና ልማትን የሚያሳይ የማያቋርጥ ጥናት አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ፡፡

 

ያነጋገርናቸው የኢኮኖሚ ባለሙያ እንደገለፁት፣ የዋጋ ንረቱ መንስኤ በትክክል አለማወቅ የሚወሰዱ እርምጃዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ በማድረግ የዋጋ ንረቱን ያባብሳል፡፡

የዋጋ ንረቱን ለመከላከል ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚን የሚያካትትና የማያቋርጥ ጥናት በኘሮጀክት በመያዝ በየመሃሉ አዳዲስ ሁኔታዎችን በመግለፅ ችግሩ ከመባባሱ በፊት እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

በነጋዴዎች መካከል ያለው ተወዳዳሪነት የተጠናከረ አለመሆንና በቁጥጥር የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ መሆን የተጨማሪ እሴት ታክስና የተርን ኦቨር ታክስ ለውጥ እንዳያመጡ እንቅፋት መሆኑንም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

በአገራችን በነጋዴዎች መካከል ያለው ውድድር አናሳ በመሆኑ በተጨማሪ እሴትና የተርን ኦቨር ታክስ ውጤት እንዳያመጡ ያግዳቸዋል፡፡ በመወሰድ ላይ ያሉት እርምጃዎች ከትክክለኛ የዋጋ ንረት መንስኤዎች ጋር ያልተያያዙ በመሆናቸው የዋጋ ንረቱን ሊያባብሰው እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

የዋጋ ንረቱ ከአቅርቦት፣ ከፍላጐት ግፊትና ከገንዘብ ፍሰቱ ጋር በተያያዘ በአንዱ ወይም የተለያዩ መንስኤዎች ውጤት ሊሆን ስለሚችልም በዚህ ላይ ሠፊ ጥናት የማድረግ አስፈላጊነትንም አብራርተዋል፡፡

በምግብ እህሎች ላይ ያለውን የዋጋ ጭማሪ መንስኤ የገቢ አቅም መጨመር ከሆነ ለመቀነስ እርምጃ መውሰድ ገበሬውን እንደሚጎዳና የከተማውን ሕዝብ የገቢ አቅም ማጠናከር የተሻለ አማራጭ እንደሆነም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የገንዘብ ፍሰቱ ጨምሯል በሚል የባንኮች የተቀማጭ ሂሳብ እንዲጨምር መደረጉ ኢኮኖሚው ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ትክክለኛ ከሆነ ችግሩን ሊያባብሰው እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

መንግሥት በብሄራዊ ባንክ ያለውን የንግድ ባንኮች የተቀማጭ ሂሳብን ከ1ዐ በመቶ ከነበረበት ወደ 15 በመቶ ማሳደግ የንግድ ባንኮች የሚሰጡትን ብድር እንዲቀንሱ ለማስገደድ የተቀመጠ ቢሆንም ኢኮኖሚያችን ከገንዘብ ፖሊሲ ጋር ብዙ የተያያዘ ባለመሆኑ በተወሰነ የከተማ አካባቢ እንጂ በአገር ደረጃ ለውጥ የማምጣት አቅሙ አነስተኛ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ከገንዘብ ፍሰቱ ጋር የተያያዙ እርምጃዎች የዋጋ ንረቱን ለማስተካከል ያላቸውን በገንዘብ አቅም ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከውጪ የሚገባ የዋጋ ንረት በተለይ ነዳጅ የሁሉንም ምርቶች ዋጋ እንደሚጨምር ይህም ከ4ዐ በመቶ በላይ የሚሆነው ምርት ከውጪ ስለሚገባ ትልቅ ለውጥ ሊፈጥር እንደሚችል አመልክተዋል፡፡ ያደጉ አገሮች ለባዮ ፊውል መስሪያነት የምግብ እህሎችን መጠቀማቸው በዓለም ላይ የምግብ እህል እጥረት በመፍጠር ዋጋውን እንዲጨምር ማድረጉ ምርትን ወደ ውጪ እንዲላክ ግፊት ቢፈጥርም የምግብ እህሎችን ወደ ወጪ መላክ የተከለከለ በመሆኑ ብዙም ለውጥ እንደማይፈጥር ተናግረዋል፡፡

በነፃ ገበያ መንግሥት ነጋዴዎችን እስከ ምን ድረስ መቆጣጠር ይችላል ብለን ለጠየቅናቸውም ሲመልሱ፣ ነፃ ገበያ ሀሳብ መሆኑንና የማህበረሰቡን ፍላጐት መሠረት ያደረገ እርምጃ መውሰድ እንደሚቻልም ገልፀዋል፡፡ ለዚህም በነፃ ገበያ በሕግ የተቀመጠ መመሪያ እንደሌለው ገልፀዋል፡፡

ነጋዴዎች በስምምነት ዋጋ የሚጨምሩበት ሁኔታ ካለ ዋጋው የማይቀንስበትን ሁኔታ አስረድተው በሌሎች አገሮች ያሉ ተመሳሳይ ችግሮችን ለመፍታት ፍትሃዊ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችን የሚቆጣጠር አካል እንዳለ ጠቁመዋል፡፡ የሚቋቋመው ኮሚሽን ተገቢ ያልሆኑ የውድድር ዓይነቶች  ተብለው የተቀመጡትን በራሱ በማጥናትና ሕጎች በማስፈፀም የገበያውን ሂደት ሊጎዱ የሚችሉትን በማጣራት እርምጃ እንደሚወስድም አብራርተዋል፡፡ በአገራችንም ተገቢ ያልሆኑ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በተለይ በስምምነት የሚደረጉ የዋጋ ጭማሪዎችን ለማስተካከል ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮችን የሚከታተል አካል በማቋቋም በትኩረት ሊሠራበት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በሌሎች አገሮች በነፃ ገበያ ያሉ የዋጋ ጭማሪዎችን ለማስተካከል ዋጋ የሚወሰንበት ሁኔታ እንደሌለ ገልፀው ከዚህ በተሻለ የግብርና ምርቶች ዋጋ ለማስተካከል ክምችት በመያዝ እጥረት ሲኖር በመሸጥ ገበያውን የሚያረጋጉበት ሂደት እንዳለና ውጤታማ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በቤዛዊት ስዩም

 
< Prev   Next >